በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ የጦር ሰራዊት ወታደሮች የሺያ ሙስሊሞች ቡድን አባላትን በጥይት ገደሉ


የናይጄሪያ እስላማዊ ንቅናቄ የተባለው ቡድን የመንግስቱ ወታደሮች በካዱና ክፍለ ግዛት ዛሪያ ከተማ ሶስት መቶ የሚሆኑ ኣባላት ገድሎብናል ሲል ተናግሯዋል።

የናይጄሪያ የጦር ሰራዊት ወታደሮች የአንድ የሺያ ሙስሊሞች ቡድን አባላትን በጥይት ገደሉ። ወታደሮቹ የተኮሱት ቡድኑ በሀገሪቱ የጦር ሃይል ኣዛዥ የአጃቢ ጉዞ ላይ ጥቃት ካካሄዱ በኋላ ነው ተብሉዋል።

የናይጄሪያ እስላማዊ ንቅናቄ የተባለው ቡድን የመንግስቱ ወታደሮች በካዱና ክፍለ ግዛት ዛሪያ ከተማ ሶስት መቶ የሚሆኑ ኣባላት ገድሎብናል ሲል ተናግሩዋል። ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የተገደሉት ሃያ ቢሆኑ ነው ይላሉ።

ተኩሱ የተቀሰቀሰው የናይጄሪያ እስላማዊ ንቅናቄ ኣባላት ባለፈው ቅዳሜ ጄነራል ቱኩር ቡራታይ ኣጃቢ መኪናዎች ሲጉዋዙ በእማኞች መሰረት መንገድ ዘግተው ድንጋይ ሲወረዉሩ ነው። የጦር ሰራዊቱ ቃል ኣአቀባይ ድንጋይ ውርወራው የጦር ሰራዊቱን ኣዛዥ ለመግደል የተደረገ ሙከራ ሲሉ ገልጸውታል።

የሺያ ሙስሊማኑ ቡድን የግድያ ሙከራ ኣልተደረገም ሲል ኣስተባብሎ ጦር ሰራዊቱ ጥቃት ያካሄደው ኣስቀድሞ ባቀደው መሰረት ነው።

ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የናይጄሪያ የጦር ሰራዊት ወታደሮች የሺያ ሙስሊሞች ቡድን አባላትን በጥይት ገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:17 0:00

XS
SM
MD
LG