በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄርያ ዮላ ከተማ በተፈጸመው የሽበር ጥቃት 30 ሰዎች ተገድለዋል


ትናንት ዮላ በተባለች ገበያ ላይ በተፈጸመው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል በትንሹ 70 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ፖሊሶችና የቀይ መስቀል ባለስልጣናት ገልጿዋል።

ካኖ በተባለችው የናይጄርያ ከተማ ላይ ሁለት ሮኬቶች ወድቀዋል ያደረሰው ጉዳት ግን አልታወቀም። ትናንት ዮላ በተባለች ገበያ ላይ በተፈጸመው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል በትንሹ 70 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ፖሊሶችና የቀይ መስቀል ባለስልጣናት ገልጸዋል። ባለፈው ወር ደግሞ ባካባቢው ካሉ ከተሞች ላይ በሚገኙ መስጊዶች በተፈጸመ የቦምብ ፍንዳታ 42 ሰዎች ተገድለዋል ከ100 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

የናይጄርያና የአጎራባች ሃገሮች ወታደራዊ ሃይሎች በአከባቢው ቦኮ ሐራም (Boko Haram) የሚቆጣጠራቸው የነበሩ በርካታ ቦታዎች ካስመለሱ ወዲህ ጽንፈኛው ቡድን በአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ላይ አትኩሯል። ቡድኑ ሰሜን ምስራቅ ናይጄርያን ለመቆጣጠር ለስድስት አመታት ያህል ሲያካሄድ በቆየው ጥቃት ምክንያት ከሁለት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል።

በናይጄርያ ዮላ ከተማ በተፈጸመው የሽበር ጥቃት 30 ሰዎች ተገድለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:00 0:00

XS
SM
MD
LG