በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር 30 የካቤኔ ሚኒስትሮች ቃለ-መሀላ እንዲፈጽሙ አደረጉ


ሳልቫ ኪርና ሪያክ ማቻ /ፎቶ - ፋይል/
ሳልቫ ኪርና ሪያክ ማቻ /ፎቶ - ፋይል/

አዲሱ የደቡብ ሱዳን የብሄራዊ አንድነት መንግስት አርብ የመጀመርያ ስብሰባውን አካሂዷል። አዲሱ መንግስት በእርስ በርሱ ጦርነት ወቅት ጠላቶች የነበሩትን ሰዎች ያቀፈ ሲሆን ሀገሪቱ እንድታገገም ከተፈልገ አብሮ መስራት ግድ ይላቸዋል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለሁለት ተኩል አመተት ያህል የእርስ በርስ ጦርነት ሲያካሄዱ ከቆዩ በኋላ ለወራት ያህል ሲጟተት የቆየውን የሽግግር መንግስት ለመመስረት በቅተዋል።

ፕረዚዳንት ሳልቭ ኪር አርብ 30 የካቤኔ ሚኒስትሮች ቃለ-መሀላ እንዲፈጽሙ አድርገዋል። ከነሱም 14 ቱ አሁን ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንት በሆኑት የአማጽያኑ መሪ ሪያክ ማቻርና በሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች የተመረጡ ናቸው።

የሽግግር መንግስት መመስረቱ ፕረዚዳንት ኪርና ማቻር በአለም አአቀፍ ተጽዕኖ ከ 8 ወራት በፊት የፈረሙትን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ወሳኝ ነው።

ማቻር ዛሬ ለሚኒስትሮቹ መማክርት ባደረጉት ንግግር በጦርነት የተበጣጠቀችው ሀገር ኢኮኖሚ እንዲያገግም ጦርነት መቆም አለበት ብለዋል።

“እንደኔ ከሆነ ይህ የሚኒስትሮች መማክርት የሚገጥመው ተግዳሮት ሀገሪቱን የማረጋጋት ጉዳይ ነው። እኛም ጉዳዩን ለሚኒስትሮቹ መማክርት ብቻ አንተወውም። የሁላችንም ስራ መሆን አለበትና።” ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኪር ደግሞ እርቅ ለማውረድ ሲባል በህዝቡ መካከል ያለውን ምሬት ወደ ጎን እንዲተው አሳስበዋል።

“ይቅር ስለመባባል ጉዳይ ያለኝ ትንሽ እውቀት እንደሚነግረኝ ይቀር ስትል ምሬቱን ትረሳዋለህ። እኛን የሚያስፈልገን ደግሞ ይህ ነው።”ብለዋል።

ሁለቱም ወገኖች የፈረሙት የሰላም ስምምነት የሽግግሩ መንግስት የኢኮኖሚና ወታደራዊ ለውጦች እንዲያደርግ፣ በሰላሳ ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሄደ እንዲሁም በእርስ በርሱ ጦርነት ወቅት የጭካኔ ተግበር በመፈጸም የሚከሰሱትን ለፍርድ በማቅረብ ተግባር እንዲተባበር ይጠይቃል።

የአፍሪቃ ህብረት የጭካኔ ተግባር በመፈጸም የተከሰሱትን ለመዳኘት ችሎት እንደሚመሰርት ባለፈው አመት አስታውቋል። መርማሪዎች ሁለቱም ወገኖች የግድያ፣ የሰቆቃ፣ የዘረፋና የጾታ ጥቃት መፈጸማቸውን እንዳረጋገጡም የአፍሪቅ ህብረት ጨምሮ ገልጿል።

ዘጋብያችን ጀሰን ፓቲንኪን ከጁባ የላከውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አውርባዋለች።

ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር 30 የካቤኔ ሚኒስትሮች ቃለ-መሀላ እንዲፈጽሙ አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG