በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሪያክ ማቻር ደጋፊ አማጽያን እና የደቡብ ሱዳን ስልጣን ክፍፍል ስምምነት


የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያኽ ማቻር [ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያኽ ማቻር [ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያክ ማቻር ደጋፊ አማጽያን ትላንት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመዲናይቱ ጁባ የተፈረመው የስልጣን ክፍፍል ስምምነት ሃገሪቱ ወደ ሰላም እንድትቃረብ የሚያደርግ አንድ ተጨማሪ እርምጃ ነው በማለት ትልቅ ስኬት እንደሆነ እየገለጹ ነው።

ትላንት ጁባ ላይ የተፈረመው ስምምነት እንዲመሰረት በታቀደው የብሄራዊ ውህደት የሽግግር መንግስት ውስጥ 30 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲኖሩ መድቧል። መንግስት 16 የሚኒስቴር ቦታዎችን ይይዛል። የገንዘብ፣ የእቅድ፣ የመከላከያ፣ የኢንፎርሜሽን፣ የብሄራዊ ጸጥታ የፍትህና የህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴሮችን ያቀፉ ናቸው።

ተቃዋሚዎቹ ደግሞ የነዳጅ ዘይት፣ የአገር አስተዳደር፣ የስራ፣ የማዕድን፣ የመሬት፣ የቤቶችና የከተማ ልማቶችን የመሳሰሉ 10 የሚኒስቴር ቦታዎችን አግኝተዋል። የውጭ ጉዳይና የመጓጓዣ ሚኒስቴነት ቦታዎች ከደቡብ ሱዳን መንግስትም ሆነ ከአመጽያኑ ጋር ግንኑነት ለሌላቸው የቀድሞ የፖለቲካ እስረኞቹ ቡድን ተሰጥቷል።

ሌሎች በደቡብ ሱዳን ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሁለት የሚኒስቴር ቦታዎች እንዳገኙ ታውቋል። የተቃዋሚው የሱዳን ህዝባዊ ሐርነት ንቅናቄ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ እዝቃኤል ሎል ጋትኩት(Ezekiel Lol Gatkuoth) ስምምነቱ የቀረቡትን ጥያቄዎች ሁሉ ባያሟልም አማጽያኑ ተቀለውታል ብለዋል።

[ፋይል ፎቶ -ከግራ ወደ ቀኝ ተቀምጠው ያሉት የደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች] የቀድሞው የደህንነት ሚኒስተር ኦያይ ደንግ አጃክ (Oyay Deng Ajak)፣ የቀድሞው የኤስፒኤል ኤም SPLM ጸሃፊ ጀነራል ፓንጋን አሙም (Pagan Amum)፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስተር ማጆክ አጎት አተም (Majok Agot Atem)፣ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ እና የደቡብ ሱዳን ወካይ በዩናትድ ስቴትስ እዝቃኤል ሎል ጋትኩት(Ezekiel Lol Gatkuoth)
[ፋይል ፎቶ -ከግራ ወደ ቀኝ ተቀምጠው ያሉት የደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች] የቀድሞው የደህንነት ሚኒስተር ኦያይ ደንግ አጃክ (Oyay Deng Ajak)፣ የቀድሞው የኤስፒኤል ኤም SPLM ጸሃፊ ጀነራል ፓንጋን አሙም (Pagan Amum)፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስተር ማጆክ አጎት አተም (Majok Agot Atem)፣ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ እና የደቡብ ሱዳን ወካይ በዩናትድ ስቴትስ እዝቃኤል ሎል ጋትኩት(Ezekiel Lol Gatkuoth)

"ባገኘነው ረክታናል ለማለት ባንችልም ይህ የፈረምንበት ስምምነት ነው። ባንረካበትም እንኳን ማንኛውንም የፈረምንበት ስምምነት እንዳለ መተግበር ይኖርብናል። ባገኘነው የመረጥናቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ደስተኞች ነን። ከአገር አስተዳደር አንስቶ እስከ የነዳጅ ዘይትና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚሂዱ የስልጣን ቦታዎች በማግኘታችን ደስተኞች ነን"ብለዋል።

አማጽያኑ ባገኝዋቸው 10 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተደሰቱት ለሰፊው የሱዳን ህዝብ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው ብለዋል ጋትኩት(Gatkuoth)።

ስምምነቱ ትልቅ ስኬት የተገኘበትና ሁሉም ወገኖች አሸናፊዎች የሚሆኑበት ነው ሲሉ ገልጸውታል። የደቡብ ህዝብ ህዝብ ሰለም ለማግኘት በትእግስት በመጠበቁም እንኳን ደስ ያለህ ብለዉታል።

ጋትኩት(Gatkuoth)አያይዘውም አማጽያኑ የምክር ቤት አባሎቻቸውን ባለፈው ነሃሴ ወር የተደረገው ስምምነት መተግበሩን ለሚከታተለው በኢጋድ ማለት በምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ትብብር በይነ-መንግስታት ለተሰየመው የጣምራ ተቆጣታሪና ገምጋሚ ኮሚሽን ማቀረባቸውን ገልጸዋል።

"ይህ ከባድ ስምምነት በመሆኑ የሀገሪትን ህዝብ እንኳን ደስ ያለህ እንላለን። ምክንያቱም አሁን በቅርቡ መንግስት ይኖረዋልና" ሲሉ የተቃዋሚዎቹ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ለቀድሞዎቹ የፖለቲካ እስረኞች የተሰጠው የብሄራዊ መንግስት ለመመስረት ባለው ፍላጎት መሰረት እንደሆነ ጋትኩት(Gatkuoth) ጨምረው ገልጸዋል።

“ሁሉም የሚኒስቴር መስርያ ቤቶች በሁላችን መካከል መከፋፈል ይኖርባቸዋል። ሁሉም ወገኖች ባገኙት ሁሉ መደሰት ይኖርባቸዋል። ሁላችንም ደቡብ ሱዳናውያን በመሆናችን ተገቢውን ውክልና ማግኘት ይኖርብናል። ህዝባችንን የማስተባበር መንፈስ ለህዝባችን ማሳይት ይገባናል። በህዝባችን ላይ ያደረስነውን ቁስል ለማካምም እርቅ ማውረድ ይኖርብናል።”

የጥምረት ተቆጣጣሪና ገምጋሚ ኮሚሽን ባወጣው የጊዜ ገደብ መሰረት የብሄራዊቅ ውህደት መንግስት እአአ በመጪው ጥር 22 ቀን መመስረት ይኖርበታል። (ከሁለት ሳምንታት በኋላ ማለት ነው።

የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደራባችን ጀምስ ባቲ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች። ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የሪያክ ማቻር ደጋፊ አማጽያን እና የደቡብ ሱዳን ስልጣን ክፍፍል ስምምነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00

XS
SM
MD
LG