በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻርን በሀገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንትነት ሰየሙ


የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖች ከሁለት ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተስማሙ ፎቶ እ.አ.አ 2015
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖች ከሁለት ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተስማሙ ፎቶ እ.አ.አ 2015

የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ሳል ቫ ኪር ተቃናቃኛቸው የሆኑትን የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻርን ትላንት በሀገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንትነት ሰየሙ። ማቻር የተሰየሙት ባለፈው ነኅሴ ወር በተፈርመው የሰላም ስምምነት መሰረት ነው።

ሪያክ ማቻር ለተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንትነት መሰየማቸውን የሰላም ስምምነቱን ወደ መተግበር የሚያመራ ጥሩ እርምጃ ነው በማለት ተቀብለውታል።

“ፐረዚዳንቱ የሰላም ስምምነቱ እንዲተገበር እንዲህ አይነቱን እርምጃ ለመውሰድ በመድፈራቸው ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። በደቡብ ሱዳን የፖለቲካ መረጋጋት ሊያመጣ ይሚችለው የስምምነቱ መተግበር ነውና። ሌላው መወሰድ ያለበት እርምጃ በጁባ ያሉት ሃይሎች ብዛት እንዲቀነስ ማድረግ ነው። አሁን የሽግግሩ የብሄራዊ ውህደት መንግስት ምስረታ እንዲጸፈም ማፋጠን ነው የሚያስፈልገው።” ብለዋል።

ዶ/ር ሪያክ ማቻር
ዶ/ር ሪያክ ማቻር

ማቻር አያይዘውም አሁን ወደ ደቡብ ሱዳን በሚሄዱበት ወቅት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍንና የፖለቲካ መረጋጋት እንዲኖር የሽግግር መንግስት መመስረት ነው ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በህዝባችን መሃል እርቅ እንዲወርድ ማድረግ ነው ሲሉም አክለውበታል።

ብዙ እቅድ ያሎት ይመስላልና ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከየት ይገኛል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው። በጦርነት ላይ የሚለው ገንዘብ ይህን ለማከናወን ያስችላል ሲሉ መልሰዋል።

ለሰብአዊ ረድኤት ከሚሰጠው ገንዘብ የተወሰነውንም በዚሁ ተግባር ላይ ማዋል ይቻላል።

ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ደቡብ ሱዳን ከጦርነት አመድ እንድትነሳ እንደሚረዳ እተማመናለሁ ብለዋል።

ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር በሀገሪቱ 28 ክፍለተ-ሀገር እንዲመሰረቱ መወሰናቸው ማቻር እንዳማይደግፉት የሚታወቅ ነው። ይህን መሰረት በማድረግ ከፕረዚዳንቱ ጋር ለመስራት ምን ያህል አመቺ ይሆናል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ኢጋድ ማለት የምስራቅ አፍሪቃ የልማት ትብብር በይነ-መንግስታት በሰጠን የውሳኔ እቅድ መሰረት ስለክፍላተ-ሀገሩ ብዛት ተዋያይተን እንድንወስን የአንድ ወር ጊዜ ሰጥቶናል። 28 በሚለው ካልተስማማን ግን ወደ ተፈረመው የሰላም ስምምነት እንመለሳለን። ስምምነቱ ደግሞ 10 ክልላት-ሀገር ነው የሚለው ሲሉ ማቻር አስገንዝበዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ጆን ታንዛ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቀርበዋለች። ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻርን በሀገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንትነት ሰየሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG