በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን መንግሥት አስከፊና መጠነ-ሰፊ የመብት እረገጣ ይፈጽማል ሲል የተ.መ.ድ. አስታወቀ

በተለይም ባለፈው ዓመት ከሚያዝያ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በሴቶች ላይ የተፈጸሙት የግዳጅ ወሲቦች፣ እጅግ ዘግናኝ እንደነበሩም፣ በድርጅቱ ሪፖርት ውስጥ ተጠቅሷል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት አስከፊና መጠነ-ሰፊ የመብት እረገጣ ይፈጽማል ሲል፣ የተመድ የሰባዊ መብቶች ቢሮ አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ቢሮው ዛሬ ዐርብ አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ፣ መንግሥቱና በውዝግቡ የተጠመዱ ወገኖች በሙሉ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ብርቱ የመብት ጥሰት እንደሚፈጽሙና ይህንንም ኃላፊነት ሊወስዱ እንደሚገባቸው አመልክቷል።

በተለይም ባለፈው ዓመት ከሚያዝያ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በሴቶች ላይ የተፈጸሙት የግዳጅ ወሲቦች፣ እጅግ ዘግናኝ እንደነበሩም፣ በድርጅቱ ሪፖርት ውስጥ ተጠቅሷል።

በተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብት ቢሮ ኃላፊ ዛይድ ራድ አል ሁሴን በሪፖርቱ ውስጥ የተጠቀሱት ጥሰቶች ለናሙና ያህል ብቻ እንደሆኑ አመልክተው፣ ዝርዝሩን ለተመለከተ ግን የዓለማችን ከፍተኛው የመብት ጥሰትና የመብት መጓደል ሊባልም ይችላል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG