በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ተቃውሚ መሪ ሪያክ ማቻር የሽግግር መንግስት ለመመስረት ከ 12 ቀናት በኋላ ወደ ጁባ እንደሚመለሱ ገልጸዋል

ፋይል ፎቶ - ከጁባ ደቡብ ሱዳን ከመኖርያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በተባበሩት መንግሥታት ደረጅት በሚገኘው ካምፕ እያለፉ
ፋይል ፎቶ - ከጁባ ደቡብ ሱዳን ከመኖርያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በተባበሩት መንግሥታት ደረጅት በሚገኘው ካምፕ እያለፉ

ማቻር የሚመለሱባትን ጊዜ ያስታወቁት ባለፈው ነኃሴ ወር የተፈረመው ውል መተግበርን ለሚቆጣጠሩት ባለስልጣኖች በላኩት ደብዳቤ ነው።

የደቡብ ሱዳን ተቃውሚ መሪ ሪያክ ማቻር ከፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር የሽግግር መንግስት ለመመስረት ከ 12 ቀናት በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ጁባ እንደሚመለሱ ገልጸዋል። በሁለቱም መካከል ያለው የስልጣን መቀናቀን ጦርነት አስከትሎ ከሁለት አመታት በላይ ዘልቋል።

የደቡብ ሱዳን ተቃውሚ መሪ ሪያክ ማቻር እ.አ.አ. 2014/ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/
የደቡብ ሱዳን ተቃውሚ መሪ ሪያክ ማቻር እ.አ.አ. 2014/ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/

ማቻር የሚመለሱባትን ጊዜ ያስታወቁት ባለፈው ነኃሴ ወር የተፈረመው ውል መተግበርን ለሚቆጣጠሩት ባለስልጣኖች በላኩት ደብዳቤ ነው።

ጁባ ከተማ ከወታደራዊ ሃይሎች ነጻ እስከሆነችበት ጊዜ ድረስና የሳቸውን ደህንነት የሚጠብቁ ወታደሮች በዋና ከተማዋ እስከሚመደቡበት ጊዜ ድረስ አልመለስም ብለው ነበር።

በደቡብ ሱዳን ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ 802 የሚሆኑ የማቻር አማጽያን ወታደሮችን ወደ ጁባ በማጓጓዝ እንደረዳ ትናንት ገልጿል።

XS
SM
MD
LG