በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማቻር አማጽያን የመንግሥት ሃይሎች ሊያጠቁን ነው ይላሉ፤ መንግሥት ግን ክሱ ከእውነት የራቅ ነው ብሏል


የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያክ ማቻር ተከታይ አማጽያን የፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር ወታደሮች በምስራቅ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያለውን ቦታችንን በማጥቃት አፋፍ ላይ ናቸው ይላሉ። አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ግን አማጽያኑ ጁባ እንዲገቡ እየተጠበቀ ነው ብለዋል።

የአማጽያኑ ቡድን ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዊልያም ጋቲያት ዴንግ በደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ሃይል ውስጥ ባለፈው ታህሳስ ወር የተደረገውን የሰላም ስምምነት እንዲተገበር የማይፈልጉ ወገጎች አሉ።

ፋይል ፎቶ - ሪያክ ማቻር
ፋይል ፎቶ - ሪያክ ማቻር

እነዚህ ወገኖች በተለይም የሪያክ ማቻር ሃይሎች በሰላሙ ስምምነት መሰረት በተመደቡልቸው ቦታዎች እንዲሰፍሩ አይፈልጉም ይላሉ ኮሎኔል ዴንግ።

“የመንግሥት ሀይሎች የሰላሙ ስምምነት መተግበርን አስመልክቶ ደስተኖች አይደሉም። ምክንያቱም አዲስ አበባ በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም ወታደራዊ ሰፈሮች በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በምስራቅና በምዕራብ ኢኳቶርያም ጭምር መከፋፋል ይችላሉ። የመንግሥት ሀይሎች ግን በከፍተኛው ናይል እንጂ በነዚህ ክልሎች ወታደራዊ ሰፈሮች እንዲኖሩ አይፈልጉም። ስለሆነም ትላንት ባገኘነው መረጃ መሰረት በሀይሎቻችን ላይ ጥቃት ለመክፈት እየተንቀሳቀሱ ናቸው።”ብለዋል

አንድ ማንነታቸው እንዲገልጽ ያልፋለጉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን በበኩላቸው የመንግሥት ሃይሎች በምስራቅ ኢኳቶርያል ክፍለ-ሀገር አጠገብ ዝር አላሉም። የአማጽያኑ መሪ ዶክተር ሪያክ ማቻርና 1,370 ሀይሎቻቸው እስካሁን ባለው ጊዜ ጁባ መግባት ስላለባቸው ይህን ላለማድረግ ነው የሚጮሁት ያሉት ብለዋል።

ይልቁንስ የደቡብ ሱዳን መንግሥት አማጽያኑ ጁባ ገብተው የአንድነት መንግሥት እንዲመሰረት እየጠበቀ ነው ብለዋል።

የማጽያኑ ቃል አቀባይ ግን ተቀዳሚው ምክትል ፕረዚዳንት ሪያክ ማቻር ሀይሎቻች ወደ ጁባ እንዲገቡ በጉጉት ይጠብቃሉ። ይሁንና በኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ በኩል ወደ ጁባ ለመግባት የኢትዮጵያ መንግሥት መፍቀድ ይኖርበታል። ምክንያቱም መለዩ የጠለቀና የታጠቀ ሃይል ጥይትና መሳርያ ጭኖ በሌላ ሉአላዊ ሃገር በኩል ለማለፍ አይችልምና።

ካላሽኒኮቭን የመሳሰሉ ቀላል ማሳርያዎችን ይዛችሁ ግቡ የሚባል ከሆነ አይሆንም። ራሳችንን ለመከላከል ስንል መላ መሳርያችንን ይዘን መግባት ይኖርብናል ይላሉ ቃል አቀባዩ ኮሎኔል ዴንግ።

የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባችን ጀምስ ባቲ የአመጽያኑን ቃል አቀባይ አነጋግሯል። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

የማቻር አማጽያን የመንግሥት ሃይሎች ሊያጠቁን ነው ይላሉ፤ መንግሥት ግን ክሱ ከእውነት የራቅ ነው ብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG