ዋሽንግተን ዲሲ —
የደቡብ ሱዳኑ አማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር ለዚያች አገር አዲስ ምዕራፍ ጅማሮ በታለመ ዕቅድ ትላንት ጁባ ላይ ዳግም የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ያደረጋቸውን ቃለ መሃላ ፈጸሙ።
ይሁንና በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው እርስ-በእርስ ያለመተማመን በቀጣዩ የሽግግር ወቅት ላይ እንዳያጠላ ሥጋት አሳድሯል። ጂል ክሬግ ከናይሮቢ ያጠናቀረችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል። አሉላ ከበደ ያቀርበዋል።
ከረዥም ጥበቃ በኃላ በመጨረሻው ትላንት ከጁባ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ሞቅ ያለ አቀባበል የጠበቃቸው የቀድሞው የደቡብ ሱዳኑ አማጽያን መሪ አዲሱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪያክ ማቻር ከተቀናቃኛቸው ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር አዲስ የጋራ መንግስት ለመመስረት ነው የተመለሱት። ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ፤