ዋሽንግተን ዲሲ —
የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊ ቡድን መሪ የሪክ ማቻር ወታደሮች በታቀደው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዛሬ ማክሰኞ ጁባ መግባታቸው አጠራጣሪ መሆኑ ተነገረ።
ይህ መርሓ-ግብር ግን፣ ባለፈው ነሓሴ ወር በጁባው መንግሥትና በSPLM መካከል የተደረሰው ስምምነት ቁልፍ ነጥብ መሆኑ ይታወቃል።
ባለፈው ሳምንት፣ የሽምቅ ተዋጊው ቡድን መሪ ማቻር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ከተማዋ ከወታደሮች ነፃ እስከሆነችና ከርሳቸው ሠራዊት የመጀሪያዎቹ 1,370ወታደሮች እስከገቡ ድረስ፤ እርሳቸውም ወደ ጁባ እንደሚመለሱ መናገራቸውአይዘነጋም።
የተቃዋሚ SPLA ወታደራዊ ቃል-አቀባይ ከሎኔል William Gatjiath እንደሚሉት፣ መንግሥት አንድ የተለየ ስፍራ ገና ስላላዘጋጀና እንደ የህክምና አገልግሎት መስጫዎችም ስለሌሉ፣ ወታደሮች እንደታቀደው ዛሬ ማክሰኞ ጁባሊገቡ አይችሉንም ብለዋል።