በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮናቫይረስ/ኮቪድ-19

እሑድ 29 ሜይ 2022

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/ኢየሱስ ትናንት ዕሁድ በተካሄደው የ75ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ንግግር ሲያደርጉ ጄኔቫ፣ ሰዋዚላንድ ግንቦት 22/2022

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ “በጣም በርግጠኝነት አላበቃም” ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/ኢየሱስ ትናንት ዕሁድ በተካሄደው የ75ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ ተናገሩ፡፡

የዳይሬክተሩ ማስጠንቀቂያ የመጣው በርካታ አገሮች እያገረሸ ባለው የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ሳቢያ ቀደም ሲል ያወጧቸውን አስገዳጅ መመሪያዎች ወደ ቦታቸው እየመለሱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

“በሁሉም የዓለም ክፍሎች በሚገኙ 70 አገሮች ውስጥ የተጋላጮች ቁጥር መጨመራቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ” ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ

“ይህ ቫይረስ ሁሌም አመጣጡ ያስገርመናል፣ ማኅበረሰቡን እየደጋገመ አሁንም አሁንም በማዕበሉ ይመታል፣ እስካሁን አቅጣጫውንም ሆነ መጠኑን ጨርሶ መገመት አልቻልንም” ብለዋል፡፡

የዓለም ጤና ድሬክተሩ በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ6ሚሊዮን ይበልጣል ያሉ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ግን ከዚህ የሚበልጥ መሆኑን ገልጾ ወደ 15 ሚሊዮን የተጠጉ ሰዎች መሞታቸውን አመልክቷል፡፡

ፎቶ ፋይል፦ ዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሁለተኛው ዩናይትድ ስቴትስ መሪነት የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ጉባዔው ባደረጉት ንግግር በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 የሚያዙ እና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም ወረርሽኙ ገና አልተወገደም፣ በሁሉም ቦታ ሳይወገድ ብቻውን ሊያበቃ የሚችልበት ስፍራ ሊኖር አይችልም ብለዋል፡፡

ከሰባ በሚበልጡ ሀገሮች እንዲያውም የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር እየጨመረ ነው የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ ነው ብለዋል፡፡

ክትባትን በሚመለከትም ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ከአንድ ቢሊዮን በላይ ያልተከተቡ ሰዎች እንዳሉ ነው ዶ/ር ቴድሮስ ያመለከቱት፡፡

በሌላ ዜና በአፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት እንዲያመርት ፈቃድ በማግኘት የመጀመሪያ የሆነው የመድሃኒት ፋብሪካ የመጣለት የክትባት ትዐዛዝ ባለመኖሩ የተነሳ በቅርቡ መዘጋቱ እንደማይቀር ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገበ።

ደቡብ አፍሪካው አስፐን ፋርማኬር ክትባቶቹን ማምረት ፈጽሞ እንዳልጀመረ ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

ኩባኒያው ከዩናይትድ ስቴትሱ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጋር የኮቪድ-19 ክትባት ለማምረት ውል ተፈራረመ ተብሎ ባለፈው ዓመት ዜናው ሲሰማ አፍሪካ ላለባት የክትባት እጥረት መፍትሄ ተገኘ ተብሎ በስፋት መወራቱ አይዘነጋም፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG