በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'መተንፈስ' ለጤና!


በሰው ልጅ የመተንፈሻ አካላት የተመሰለ እና ለአተነፋፈስ ስርዓትታችን ማሳያነት የተሰራ ምስል
በሰው ልጅ የመተንፈሻ አካላት የተመሰለ እና ለአተነፋፈስ ስርዓትታችን ማሳያነት የተሰራ ምስል
'መተንፈስ' ለጤና!
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:12 0:00

ቀላል እና ያለ አንዳች ሃሳብ ቀኑን በሙሉ ሳናቋርጥ የምናደርገው ድርጊት መሆኑ፣ ኃያል የሕይወት ምስጢርነቱን ለመዘንጋት ያቃርበናል። በተፈጥሮ ልማድ ከማድረግ ያለፈም አስክናጣው ድረስ የሚገባውን ዋጋ የሚመጥን ቦታ አንሰጠውም።
በአንዲት ቀን ውሎ ብቻ በአማካይ ፳ ሺሕ ለሚጠጋ ጊዜ ያለ አንዳች የተለየ ጥረት ማድረጋችን፤ አየር ስበን ወደ ሳምባችን እናስገባ እና ከሳምባችን ያለውን የቀደመውን ትንፋሽ እንለቀዋለን። እናም ሌላ ትኩስ አየር መማግ ... የማይቋረጠው ዑደት ይቀጥላል።

ዶ/ር ሰላም አክሊሉ
ዶ/ር ሰላም አክሊሉ

"በደመ ነፍስ" ሊባል በሚችል ዘይቤ የምንፈጽመውን ድርጊት፣ ሆን ተብሎ እና በአግባቡ ወደ ሚደከናወን የአተነፋፈስ ዘዴ ስንወስደው ግን፤ 'መተንፈስ' ለጤና ተጀመረ ማለት ነው። ካሁን ቀደም ይበልጡን የምሥራቁ ዓለም ፍልስፍና አይነተኛ ዘዬ የነበረው ጥበብ ወደ ዘመናዊው ሳይንስ ዓለም ከዘለቀም ሰነብባቷል።

“’የአተነፋፈስ ልማዳችንን ማሻሻል’ .. 'ከቀልባችን የመሆንን ያህል ቅርብ ነው' ይሉናል፤ ባለ ሞያዋ እንግዳችን ዶ/ር ሰላም አክሊሉ። በልዩ ትኩረት ሚልዮኖችን የመድረስ እና የማስተማር ውጥንም አላቸው። መሰንበቻውን ወደ ስቱዲዮችን ጎራ ባሉበት ወቅት ስለ ሳይንሱም ስለ ውጥናቸውም በሰፊው አጫውተውናል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG