“ጆሮዬ ላይ ጭው የሚል ኃይለኛ እና አዋኪ ድምጽ፣ ለየት ያለ ድምጽ ይሰማኛል” ሲሉ ሰዎች በተለያየ መልክ የሚገልጹት ችግር ነው።
ይሁን እንጂ የተለያዩ ሰዎች የሚሰማቸው ድምጽ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል ባለሞያ ዎች ያስረዳሉ።
“በእንግሊዝኛ በሕክምናው አጠራር ‘tinnitus’ በመባል የሚታወቀው ይህ ሁኔታ የሚከስታቸው ድምጾች እጅግ ብርቱ ወይም ቀላል ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት ለሞያዊ ማብራሪያ የጋበዝናቸው የአንገት በላይ ልዩ ሃኪም እና የሕክምና መምሕሩ ዶ/ር በላቸው ተሰማ ናቸው።
“የሚያቃጭል፣ ወይም ‘ጥዝዝ’ የሚል፣ እንደ ነፋስ ያለ አለያም ሌላ ለየት ያለ ድምጽ ሊሰማም ይችላል’ ይላሉ። ቁጥሩ ከ15 እስከ 20 በመቶ የሚሆን ሰው የሚያጠቃ እና በጣም የተለመደ ነው።
የማለሞያውን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም