በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ የሕክምና መጀመሪያ እና መጨረሻ


ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሃኪም ሚነሶታ ዩናይትድ ስቴትስ
ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሃኪም ሚነሶታ ዩናይትድ ስቴትስ

በአመዛኙ የሚገባውን ሥፍራ የተነፈገ ቁልፍ የሕክምና ዘርፍ ነው፡፡ ከልብ እና የሆድ እቃ የሕመም አይነቶች፣ ጭንቀት እና የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የስኳር በሽታ አለያም በደም ውስጥ የስብ መጠን ከፍ ማለት - ሁሉም በአናኗር ዘይቤ ለውጥ ይረዳሉ።

የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ የሕክምና መጀመሪያ እና መጨረሻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:11 0:00

“ብዙዎቹ እነዚህ መድሃኒቶች ተጠንተው ‘በሽታውን ይፈውሳሉ’ ተብለው መጀመሪያውኑ ሲታሰቡ፣ የኑሮ ዘይቤ ለውጦችም በዚያ ሙከራ ወቅት አብረው ተጠንተው ነው ለሕክምናው እንዲውሉ የሚደረጉት። ይህም ማለት ለአንድ ሰው ዝም ብለን መድሃኒቶች ብቻ በምንሰጥበት ወቅት ከሚያስፈልገው የሕክምና እንክብካቤ ቀንሰን እንደመስጠት የሚቆጠር ነው። ለዚህም ምክኒያቱ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ባለመካተቱ!” ሲሉ የልብ በሽታዎች ልዩ ሃኪሙ ዶ/ር ውብሸት አየነው ያስረዳሉ።

አንዳንድ የሕመም አይነቶችም “ማድረግ ያለብንን ባለማድረግ፣ የሌለብንን ደግሞ በማድረግ” የሚከሰቱ መሆናቸውን ያብራሩት ዶ/ር ውብሸት እዚህ ላይ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ያለውን ፋይዳም ተንትነዋል።

ዶ/ር ውብሸት በሚኔሶታ ክፍለ ግዛት የሚገኘው ሄነፒን የህክምና ተቋም የልብ ሕክምና ክፍል ድሬክተር ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG