እንደ ብርቱ የጤና ችግር የሚታየው "እጅግ ከፍተኛ" የሰውነት ክብደት፣ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ልዩ ልዩ የጤና ጠንቆች እንዳሉ ይታመናል።
በሕክምናው ዓለም የእንግሊዘኛው አጠራር ‘ኦቤሲቲ’ በመባል የሚታወቀውን ይህን ‘እጅግ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት’ በማከሙ ረገድ፣ "ከአሁን ቀደም ያልታየ" የተባለን ውጤት ያሳዩትና ከፍተኛ ትኩረት የሳቡት እነኚኽ መድኃኒቶች፥ “የጥቅማቸውን ያህል በሐኪም የቅርብ ክትትል እና በጥንቃቄ መወሰድ ያለባቸው ናቸው” - እንደ ባለሞያዎች ማብራሪያ።
የምሽቱ "ሐኪምዎን ይጠይቁ" ዝግጅት፣ ይኸው የጤና ችግር በሕክምና የሚረዳባቸውን መድኃኒቶች ምንነት፣ ፋይዳ እና ፈተናዎች የሚፈትሽ የባለሞያ ትንታኔን ይዟል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለሞያው ዶክተር አቤል ተካ ናቸው።
መድረክ / ፎረም