በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?


ዶ/ር አቤል ተካ - የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሃኪም - 'ሴንታራ ሄልዝ' የሕክምና ተቋም - ቨርጂንያ
ዶ/ር አቤል ተካ - የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሃኪም - 'ሴንታራ ሄልዝ' የሕክምና ተቋም - ቨርጂንያ

በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል ይሆን? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተደረሰባቸው ያሉ ከበሽታው ጋር የተዛመዱ ሁኔታዎች ካሁን ቀደም ስለሕመሙ ይታመኑ የነበሩ እውነታዎችን ጭምር በእጅጉ እየቀየሩ መሆናቸው ይነገራል።

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

"ለመሆኑ ከስኳር በሽታ ሙሉ በሙሉ ሊዳን ይችላል?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “አዎንም፣ አይደለምም፤ ነው” የሚሉን ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለ ሞያው ዶ/ር አቤል ተካ ናቸው።

”‘ኢንሱሊን’ የተባለውን ሰውነት የሚያመነጨውን ንጥረ ነገር የሰውነት አካላት በአግባቡ መጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር በወጉ መረዳት፤ የተለያዩ ውስብስብ ችግሮች የሚያስከትለውን የስኳር በሽታ ምንነት ለመረዳትም ሆነ፤ በሽታውን ለማከም በሚሰጠው ሕክምና እና ሕመምተኛው በራሱ ሊያደርጋቸው በሚችላቸው ጥረቶች አመርቂ ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ነው” ይላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG