ዋና መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው “ፒፕል ቱ ፒፕል” ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የአርሊንግተን ዋና ከተማ የተመሰረተበትን ሃያ አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ዓመታዊ የሕክምና ሳይንስ ጉባኤው አካሂዷል። አብዛኞቹ አባላቱ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሞያዎች ቢሆኑም፤ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የሕክምና ባለ ሞያዎችም ለዓመታት ተሳትፈውበታል።
ከሕክምና አገልግሎቶች እና የህክምና ትምሕርት ተሳትፎዎቹ በተጨማሪም በሌሎች ርዳታ የሚሹ ማኅበራዊ ጉዳዮች አስተዋጽኦ ሲያደርግ የቆየ ድርጅት ነው። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ከድርጅቱ አመራር አባላት ጋራ ውይይት አካሂደናል።
ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም