በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራሲ በተግባር


ዴሞክራሲ በተግባር

በምዕራብ ወለጋ አይራ ወረዳ ሰሞኑን አሰቃቂ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን ምስሉ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሲታይ የነበረ አንድ ወጣት ወንድማቸው መሆኑን ያመለከቱ ግለሰብ ወጣቱ “በፀጥታ ኃይሎች ነው የተገደለው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የአይራ ወረዳ ፀጥታና አስተዳደር በበኩሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ ወጣቱ በወንጀል ተጠርጥሮ የሚፈለግ የነበርና በቁጥጥር ሥር ውሎ ከዋለ በሁዋለ ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርግ መገደሉን አመልክቷል።

በሌላ ዜና በደቡብ ሕዝቦች የሰገን ዞን እንዲፈርስ የተወሰደውን ወሳኔ ተከተሎ የዞኑ ሰራተኞች መበተናቸውንና የደመወዝ ክፍያም ተነፈግን ሲሉ አማረሩ።

የክልሉ የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በበኩሉ የ610 ሰራተኞችን ምደባ በተመለከተ የማስተባበር ላይ ይዣለሁ፤ የደሞዝ ክፍያው ይፈፀም ግን በቅድሚያ የስራ መደብ ልሰጣቸው ይገባል እያለ ነው። ቅሬታቸው ተገቢ ነው። ወደ ሥራቸው የሚመለሱበትም ጥረት ተጀምሯል ነው የተባለው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዴሞክራሲ በተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:13 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG