በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሃዋሳ የወንጀል ድርጊቶች ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው ነዋሪዎች ገለፁ


በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ክልሉን እያስተዳደረ ካለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስፈፃሚ ዕዝ ጋር የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተወካዮች ትናንት በየተወያዩበት ወቅት ወታደራዊው ዕዝ እንዲያበቃና የመከላከያ ሠራዊትም ከከተማው እንዲወጣ የጠየቁ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ “የለም መቆየት ሠራዊቱ መቆየት አለበት፤ ሰላም ያገኘነው ወታደራዊ ዕዙ፣ የመከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከተማዪን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ነው” ያሉም ነበሩ።

ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ እንደሚወጣ፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ እንድሚችል ዕዙ አስታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሃዋሳ የወንጀል ድርጊቶች ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:03 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG