በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የኤጄቶ መሪዎች" በዋስ እንዲለቀቁ ፍ/ቤት ወሰነ


በሀዋሳ ከተማና ሲዳማ ዞን ሐምሌ 11 በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ፤ በተለምዶ "የኤጄቶ መሪዎች" የሚባሉ ግለሰቦች እያንዳንዳችው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንድለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰኔ አስተላለፈ፡፡

ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ለ14 ቀናት እንዲራዘም ያቀረበውን ጥያቄ ጉዳዩን የሚያየው የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት አልተቀብለውም፡፡

ዳሩ ግን ፖሊስ ይግባኝ ማለት እንድሚችል ገልጦ፤ ለነሃሴ 14/2011 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የሲዳማ ዞን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ በዞኑ ተከስቶ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከሥልጣን በታገዱት የዞኑ አስተዳዳሪ ቃሬ ጫውቻ ምትክ የተሾሙትን የአቶ ደስታ ሌዳሞን ሹመት አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በህግ የበላይነት፣ በፀጥታ፣ በወቅታዊ ሁኔታዎችና በውሳኔ ሕዝብ አፈፃፀም ሂደት ዙሪያ መምከሩንም አፈ-ጉባዔው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"የኤጄቶ መሪዎች" በዋስ እንዲለቀቁ ፍ/ቤት ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG