በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ጋር የተደረገ ውይይት


አርአያ ገ/እግዚ አብሄር መሐሪ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
አርአያ ገ/እግዚ አብሄር መሐሪ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

“እኛ የሠራነውና የመጣው ውጤት የተራራቀ ነው” ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ዛሬም የቅሬታ ቅጽ ሲሞሉ ውለዋል። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ትምሕርት ቤቶች በፈተና ሂደቱ ላይ የነበረው ችግር ሳይስተካከል ውጤቱ ይፋ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።

አገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ገብረእግዚያብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ሁኔታውን ሲያስረዱ፤ ስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት በተሰኘው ፈተና ላይ የእርማት ችግር መፈጠሩን ተረጋግጧል። ፈተናውን ለሚያርመው ማሽኖች የተሰጡት የመልስ ቁልፎች ቦታ በመቀያየራቸው ከ319ሺሕ ተፈታኞች ግማሽ በሚሆኑት ውጤት ላይ ስህተት ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ነው፤ ያብራሩት።

የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ቀረበ የተባለው ቅሬታም “ለእኛ አልደረሰንም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ኤጀንሲው በአማራ፣ በኦሮሚያ በደቡብና በቤንሻንጉል ክልሎች የሚገኙ 848 ተማሪዎች ውጤት ይዞ እያጣራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት የተፈጠረውን የእርማት ችግር በመፍታተ የተስተካከለው ውጤት በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በሌሎች ተማሪዎች እየቀረበ ያለውን ቅሬታ በተመለከተም “ጭብጥ ያለው ከሆነ እናያለን” ሲሉ አረጋግጠዋል።

የፈተናውን ውጤት አስመልክቶ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተያየት መስጠት መብት መሆኑን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰጡ አስተያየቶች ግን መረጃን ብቻ መሰረት እንዲያደርጉ መክረዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ጋር የተደረገ ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:05 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG