በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ መቀጠሉ ተገለፀ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡ ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገርም ትክክል አይደለም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡ የተወሰ ጊዜም እንደሚወስድ ይታወቅ እንደነበርም አብራርተዋል፡

ፖሊስ በጅምር ላይ የነበረውን ምርመራ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱን ያስታወሱት ኮሚሺነሩ፣ ሲጠናቀቅም ለሚመለከተው አካልና ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ኮሚሺነሩ አክለው እንዳሉትም ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ከታሰሩ ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ቁጥርም ከመቶ እንደማይበልጥ አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሁ ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር፣ በመንግሥት ከሚገልፀው የበለጠ መሆኑን እንደሚናገሩ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሺነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰውን በስልክ አነጋግረናቸዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ መቀጠሉ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG