በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚኒስትሩ በሩቅ ምሥራቅና በእሥራኤል


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮሪያ ጃፓንና እሥራኤል ያደረጉት ጉብኝት ለ2012 የተያዘውን ሦስት ሚሊዮን የሥራ ዕድል የመፍጠር ዕቅድ የሚያግዝ መሆኑን ቃል አቀባያቸው እስታወቁ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ጉብኙቱ ከሥራ ፈጠራ እና ከኢንቨስትመንት አንፃር የኢትዮጵያን ምቹ ሁኔታ ለማሳየት የተቻለበት ነው።

የሁለትዮሽ ስምምነቶች የተፈረሙበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እና በእሳቸው የሚመራው የለውጥ ሂደት የተነሳበት መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ገልፀዋል።

ለሁለት ተከፍሎ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ወደአንድ እንዲመጣ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሁንም ለመሰል የሰላም ሚና ዝግጁ መሆናቸውንም ቃል አቀባያቸው ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒትሩ በቅዱስ ሲኖዶስና በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ይሸመግሉ እንደሆነ በአሜሪካ ድምፅ የተጠየቁት ቃል አቀባያቸው ከተጋበዙ ዝግጁ ናቸው ነው ያሉት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ዘርፍ ኃላፊ የሆኑትንና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተጉዘው የተመለሱትን ቢልለኔ ስዩምን አነጋግረናቸዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠ/ሚኒስትሩ በሩቅ ምሥራቅና በእሥራኤል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:38 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG