በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጫልቱ ታከለ ተፈታች


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሻምቡ ከተማ በማዘዣ ማዕከል ተይዛ ለሥድስት ቀናት እስር ላይ የቆየችው ጫልቱ ታከለ መፈታቷ ታወቀ።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሻምቡ ከተማ በማዘዣ ማዕከል ተይዛ ለሥድስት ቀናት እስር ላይ የቆየችው ጫልቱ ታከለ መፈታቷ ታወቀ። ባለፈው ማክሰኞ ለጥያቄ መወሰዱንና ከጥቂት ቆይታ በኋላ እንደተፈታ ዘግበን የነበርነው የጫልቱ ወንድም ሰኚ ታከለ ግን ዛሬ አመሻሹን መታሰሩ ተሰምቷል፡፡

ሌሎች ሰዎች አለመፈታታቸውንና የታሰሩ መኖራቸውንም የሻምቡ ነቀምቴና ጊምቢ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የምዕራብ ወለጋ ዞን አሰተዳዳሪ ሰሞኑን ተከስቶ ነበረው ያለመረጋጋት ችግር ጋር በተያያዘ ሰዎች ቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆናቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

የሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮችን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጫልቱ ታከለ ተፈታች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG