በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ወባን በማጥፋት የላቀ ውጤት በማምጣቷ ተሸለመች


በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራን ቋሚ ልዑክ አንደኛ ፀሐፊ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ አቶ ቢንያም በርሀ የአልማውን ሽልማት እየተቀበሉ
በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራን ቋሚ ልዑክ አንደኛ ፀሐፊ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ አቶ ቢንያም በርሀ የአልማውን ሽልማት እየተቀበሉ

የፀረ ወባ ጥምረት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሀገሮች ሽልማት ሰጠ። ኤርትራ ከተሸለሚ ሀገሮች አንዷ ነች።

የአፍሪካ መሪዎች ፀረ ወባ ጥምረት (አልማ በሚል ምኅፃርም ይታወቃል) ባለፈው ጥር 21 አዲስ አበባ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽ/ቤት የሽልማት ሥነ-ስርዓት አካሄዶ ነበር።

ዓላማው የወባ ወረርሽኝን ከአፍሪካ ለማጥፋት የሆነው አልማ፣ እ.አ.አ. የ2016 ወባን ለማጥፋት በተያዘው ዓለምአቀፍ ዘመቻ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና ለተሳካላቸው ሀገሮች ሽልማት ሰጥቷል።

ኤርትራ በላቀ ውጤታቸው ከተሸለሙት ሀገሮች አንዷ ነች። እንዲሁም ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ናሚቢያ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዋዚላንድ አና ሳኦ ቶሜም በተመሣሣይ ውጤት ተሸልመዋል።

የአፍሪካ መሪዎች ፀረ ወባ ጥምረት (አልማ)፣ ዓላማው የወባ ወረርሽኝን ከአፍሪካ ለማጥፋት ነው። እ.አ.አ. የ2016 ወባን ለማጥፋት በተያዘው ዓለምአቀፍ ዘመቻ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና ለተሳካላቸው ሃገሮች ሽልማት ሰጥቷል።
የአፍሪካ መሪዎች ፀረ ወባ ጥምረት (አልማ)፣ ዓላማው የወባ ወረርሽኝን ከአፍሪካ ለማጥፋት ነው። እ.አ.አ. የ2016 ወባን ለማጥፋት በተያዘው ዓለምአቀፍ ዘመቻ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና ለተሳካላቸው ሃገሮች ሽልማት ሰጥቷል።

በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራን ቋሚ ልዑክ አንደኛ ፀሐፊ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ አቶ ቢንያም በርሀን ባለፈው ሳምንት በስልክ አነጋግረናቸው ነበር። ስለ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱና ስለ ኤርትራ በወባ ወረርሽኝ ላይ ያላትን ፖሊሲ ሲገልጹ፣ "የኤርትራ የፓሊሲ እድገት ህዝቡን አስቀድሞ ግምት ወስጥ የሚያስገባ ስለሆነና ፖሊሲው በህዝብ ተሳታፊነት ስለሚተገበር ነው" ብለዋል። አክለውም፣ "ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቀዳሚነት የሚሰጠው የትምህርት፣ የጤና፣ መንገዶችን መገምባት፣ ንጹህ የሚጠጣ ውሃ ማቅረብ የመሳሰሉትን ነው። እነዚህ ጥረቶች ተደምረው ብዙ የሚለንየም እድገት ዓላማዎችን ለመምታት (MDGs) እንደተቻለና የኤርትራን እድገት አጉልቶ ለማሳየት ተችሏል" ይላሉ ።


የተባበሩት መንግስታት ልዩ ወኪል በጤና እድገት ላይ እናም በወባ ወረርሽኝ ዘመቻ ላይ ገንዘብ የሚመድቡት ልኡክ ሬይ ቼምበርስ በበኩላቸው፣ እ.አ.አ 2015 የተካሄደው በአፍሪካ ውስጥ የወባ ማጥፋት ዘመቻን ጠቅሰው፣ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የጤና ጥበቃ ሰራተኞች ጥረት ወሳኝ መሆኑን ይገልጻሉ።

"እነዚህ ሁሉ ጥረቶች መድሃኒት መርጨትም ሆነ መድሃኒት ለታመሙት ማቅረብ እደተጀመረው ከቀጠለ፣ አፍሪካ ውስጥ ከ100 ሽህ በላይ ወይም ደግሞ በበሽታው ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ወደ ዜሮ ለማስጠጋት፣ የህፃናትን ሞት በዓመቱ መጨረሻ ላይ መቀነስ ይቻላል ብዬ አምናለሁ። ይህም ማለት፣ ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ ወረርሽኙን በ92 ከመቶ መቀነስ ማለት ነው" ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዘገባ እንደሚገልጸው በወባ ወረርሽኝ ምክንያት አፍሪካ ውስጥ ወደ 437 ሽህ ህፃናትና 163 ሚልዮየን የሚሆኑ ሰዎች በየዓመቱ በበሽታው እንደሚጠቁ ነው ነው። ወደ 80 ከመቶ የሚሆኑ ሰዎች እስካሁን በወባ ምክንያት መሞታችውንም ዘገባው ይጠቁሟል።

እስካሁን ድረስ በዓለም ደረጃ የወባ ወረርሽኝን ለመቀነስ በተደረጉት ጥረቶች በወባ ህመም የተጠቁ ሰዎች ቁጠር በ34 ከመቶ ሲቀንስ፣ በወባ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 54 በመቶ መቀነሱን የተባበሩት መንግሥታት ዘገባ ገልጿል።

በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራን ቋሚ ልዑክ አንደኛ ፀሐፊ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ አቶ ቢንያም በርሀን ባለፈው ሳምንት በስልክ አነጋግረናቸው ነበር። ኤርትራ የላቀ ውጤት በዚህ ዓመት ብታመጣም አብዛኛውን ጊዜ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስትቀርብ በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ያተኮረ ዘገባዎች ላይ ነው። አቶ ቢንያም ስለዛም ሆነ ስለ ሽልማቱ ምን አስተያየት እንዳላቸው በዝርዝር ገልጸውልናል። ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ኤርትራ ወባን በማጥፋት የላቀ ውጤት በማምጣቷ ተሸለመች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00

XS
SM
MD
LG