በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዞን ዘጠኝ ከአፍሪቃ ተመርጠው የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኅን ነፃነት ሽልማት ተሸለሙ


የዞን ዘጠኝ አባሏ ወ/ት ሶልያና ሺመልስ
የዞን ዘጠኝ አባሏ ወ/ት ሶልያና ሺመልስ

የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ድርጅት(CPJ) ትናንትና ማታ በዓለም አቀፍ ዙሪያ መረጃ የብዙኅን ነፃነት እንዲከበር ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ሽልማት በኒው ዮርክ አበረከተ።

የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ወይም በእንግሊዝኛ ምኅፃር ስሙ ሲፒጄ (CPJ) እየተባለ የሚታወቀው ድርጅት ትናንትና ማታ በዓለም አቀፍ ዙሪያ መረጃ የማግኘት ነፃነት፣ ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት፣ የመገናኛ ብዙኅን ነፃነት እንዲከበር ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ሽልማት አበርክቷል።

ከነዚህም ውስጥ ትናንት ምሽት የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች የመናገር ነጻነት በኢትዮጵያ እንዲከበር በመስራታቸው ከመላ አፍሪቃ ተመርጠው የዓለም አቀፉን ሽልማት በስነስርአቱ ተቀብለዋል።

የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች በፀረ-ሽብር ሕጉ ህዝብን በማነሳሳት በኢትዮጵያ መንግሥት ክሥ ተመስርቶባቸው መታሰራቸውና መንገላታታቸውን የተለያዩ የመብት ድርጅቶች ሲያሳስቡ ቆይተዋል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት በዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችና በሶት ጋዜጠኞች ላይ የመሰረተውን ክስ አቋርጦ ከወኅኒ ቤት ለቋል።

የዞን ዘጠኝ አባሏ ወ/ት ሶልያና ሺመልስ በስነስርአቱ ተገኝታ የሰጠችውን ንግግር ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ።

ወ/ት ሶልያና ሺመልስ ጸሀፊዎቹ በዌብ ሳይታቸው ሕገመንግሥታዊ መብቶች እንዲከበሩ እስከዛሬ እየሰሩበት ያለ ጉዳይ መሆኑን ገልጻለች። በጋዜጠኞች መብት ላይ ያላትን ሃሳብና ለኢትዮጲያ መንግስትም ሆነ ለሌሎች ሃገሮች ይሆናል የምትለውን ጥሪ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ተችታለች።

ከስነስርአቱ በኋላ በስልክ ሳሌም ሰለሞን አነጋግራት ነበር ቃለ ምልልሱን ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ዞን ዘጠኝ ከአፍሪቃ ተመርጠው የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኅን ነፃነት ሽልማት ተሽለሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:26 0:00


XS
SM
MD
LG