የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ወኪል ፈረደሪካ ሞግሪኒ (Federica Mogherini)ባለፈው ሳምንት ኢትዮጲያን ጎብኝተው ነበር። ጉብኝታቸው የአውሮፓ ሕብረትን እና የኢትዮጲያን ግንኙነት አርባኛ ኢዮቤልዩ አስመልክቶ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ጉባኤ ላይ ሕብረቱ ከአፍሪቃ እና ከኢትዮፕጵያ ጋር ያለውን አሰራር ለማዳበር የሚችልበትን ሁኔታዎችን በማንሳት ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን በመወሰኛው ምክር ቤት ምርመራ ኰሚቴ ፊት ቀርበው፣ በቤንጋዚ-ሊብያ ከየዩናይትድ ስቴትስሱ አምባሳደር ግድያ ጋር በተያያዘ የምስክርነት ቃላቸውን እየሰጡ ናቸው።
ባለፈው ነኀሴ ሜዲቴራኒያን ባህርን ለመሻገር ከተሣፈረችበት ጀልባ ባወጣት የጀርመን የባህር ኃይል መርከብ ላይ የተገላገለችው ሶማሊያዊት ስደተኛ ፍልሰተኞችን በሚያሸጋግረው ጀልባ ላይ የተሣፈርኩት “ከነፅንሴ ብሞትም ልሙት ብዬ ነው” ብላለች።
እሥራኤል ውስጥ ትናንት የተገደለው ኤርትራዊ የሞተው በተተኮሰበት ጥይት ምክንያት መሆኑን ቀዶ ሕክምናውን የሠሩት ሃኪም ገልፀዋል፡፡
ኤርትራ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል ጥረት እያደረገች መሆንዋ ታውቋል።
የአውሮፓ ሕብረት 28 አባሎች ወደ 160 ሽህ የሚጠጉ ስደተኞችን ወደ ሌሎች አባል ሃገሮች ለማስፈር ተስማሙ።
ለዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊው ቄስ አባ ሙሴ ዘርዓይ ታጭተዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች የመጡ ወደ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችና ስደተኞች፣ በደቡብ ጣልያን የተባበሩት የአውሮፓ የባሕር ሃይሎች ከመስመጥ አድነዋቸዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኤርትራና የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች ባደረጉት ንግግር ሁለቱም አገሮች በድርጅቱ የተጣለባቸውን የኢኮኖሚና የጦር እገዳ እንዲነሳላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ኤርትራን ወክለው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ሰባኛ ጉባኤ የተሳተፉት አባሎች
የዓለም አቀፍ ድረ ገጽ ጋዜጠኞች በተ.መ.ድ. ጠቅላላ ሰባኛ ጉባኤ ላይ ዘገባቸውን ከዚህ የድረ ገጽ ማእከል ነበር የሚልኩት።
የአኅጉራዊና የሰሜን አፍሪቃን አከባቢ ፀጥታ ለማረጋገጥ በሊብያ ሰላም መስፈን እንዳለበት መሪዎች ሃሳባቸውን ገልፀዋል።
በሊብያ ያተኮረ የሚኒስተሮችና ከፍተኛ መሪዎች የጎን ስብሰባ
“ይህ ቀውስ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ እልቂትና ፍልሰት ነው።” ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን በ70ኛው ጉባኤ ትናንት እሮብ ስለ ፍልሰተኞች እና ስደተኞችን በተመለከተ ከዓለም መሪዎች ጋር መክረዋል።
የዞን ዘጠኝ ፀሐፊዎች የዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሸላሚ እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡