በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ጉባዔ በአዲስ አበባ (እአአ 2016)


የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:29 0:00

የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ

የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ዳይረክተር ሶንያ ሩትዘል (Sonja Ruetzel) የመድረኩን ዓላማና እአአ በየካቲት ሁለትና ሦስት በአዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማእከል የስብስባ ፕሮግራሙን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ዓላማ ለተፈጥሮ ቀዉስ እርዳታ ማቅረብና ተጎጂዎች ቀዉሱን እንዲቋቋሙ ማስቻል ነዉ። ይህንንም የሚሰራዉ ከብዙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላትና እንደ ቀይ መስቀል ያሉ ክልላዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ተቋማት፥ የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የትምህርት ተቋማትና ሌሎችም ጋር በመተባበር ነዉ። ድርጅቱ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ጉባኤ ሲያዘገጅ ሰባተኛ ዓመቱ ነዉ። ድርጅቱ ከተመሰረተ ግን አስራ ሶስት ዓመታት አስቆጥሯል።

ስለዚህ ዋናዉ ዓላማ ለተሻለ የሰብአዊ የእርዳታ አቅርቦትና ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም፣ ድርጅቶች ልምድ እንዲለዋወጡና ማስቻል ነዉ። በዚህም ዓላማ በፊታችን የአዉሮፓዉያን የካቲት ሁለትና ሶስት አዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማእከል ዉስጥ ስብስባ ይኖረናል።

የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ጉባዔ በአዲስ አበባ (እአአ 2016)

በዚያ ስብሰባ ላይ ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ በተለያዪ መስኮች እዉቀት ያላቸዉ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ፕሮግራም አዘጋጆቹ ይጠብቃሉ። ስብሰባዉም ስለ ተፈጥሮ ቀዉስና ቀዉሱን መቋቋም ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ እንደ ምግብ ዋስትና፣ የዉሃ አቅርቦት፥ ጤና ጥበቃን የመሳሰሉ ርእሶችን ይጠቀልላል።

የስብሰባውን አጀንዳ ለማምበብም ሆነ ለመሳተፍ ይህንን ፋይል በመጫን የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክን(AIDF)ዌብ ሳይት ይጎብኙ።

XS
SM
MD
LG