በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአይቮሪ ኮስት ፕረዚደንት ድህነትን በግማሽ ለመቀነስ እንደሚጥሩ አስታወቁ


ፕረዚደንት አላሳን ዋታራ የአይቮሪ ኮስት ብሔራዊ ምርጫን ሰማንያ ሶስት ከመቶ በማሽነፍ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸው ከ5ቀናት በፊት ይፋ ሆኗል።

በሚቀጥለው የስልጣናቸው ዘመን፣ አላሳን ዋታራ፣ በሀገሪቱ ድህነትን በግማሽ ለመቀነስና፤ ብሔራዊ እርቅ ለማስፈን እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።

በ2003 ዓ.ም. በአይቮሪ ኮስት በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ላይ በተነሳው ግጭት ፣ ወደ ሶስት ሽህ የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው ምርጫ ግን ሰላማዊ እንደነበረ ተገልጿል።

የፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ፓስካል አፊ ንጉሳን (Pascal Affi N'Guessan)፣ ሀገሪቱ ካለፈው ምርጫ ማጥ ለመውጣት በምታደርገው ጥረት፤ የህዝቧ መከፋፈልን ካልፈታች ወደፊት ችግር እንደሚፈጥር ይገልጻሉ። አላሳን ዋታራ የምርጫውን ሂደት እንዲህ ይገልጹታል።

“ምርጫው በጣም ጥሩ ነበር። ግልጽ፣ ተዓማኒና በዲሞክራሲያዊ በሆነ ሂደት ስለተፈጸመ ግሩም ነበር። ከዚህ በፊት የተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ሁከት የሞላበት ስለነበር፤ ከአሁኑ ምርጫ ውጤት ብዙ መሻሻሎችን ጠብቄ ነበር” ብለዋል።

ቀጥለውም፣ “ለሃገሬ አዲስ ሕገመንግስት ብመሰርት በጣም ደስ ይለኛል። የህዝቡን ህይወት ማሻሻልና ለወጣቶች እድል መፍጠር በጣም አስፈላጊ ነው። ሃገሪቷ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍንባት እጥራለሁ። በኮትዲቯር የስልጣን ዘመኔ ሲያበቃ ማየት የሚፈልገውም ሀገራችን የዲሞክራሲ ሞዴል እንድትሆን ነው” ብለዋል።

ጥሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና ሁኔታ ሕዝባዊ መግባባትን እንደሚያስከትል እየተመለከትን ነው። ከዚህ በፊት ካየነው ቀውስ፣ የዛሬው ምርጫ ከ 50 በመቶ የሚሆኑ ሰዎችን ያሳተፈ ሰላማዊ መሆኑ እድገትን ያሳያል። ለሚመጣው ትውልድ ይህንን አካሄድ መቀጠል አለብን።
የአይቮሪ ኮስት ፕረዚደንት አላሳን ዋታራ

የአይቮሪ ኮስት የሕገ መንግስታዊ ፍርድቤት የምርጫውን ውጤት አጣርቶ ከአንድ ሳምንት በኋላ አሸናፊውን ለማረጋገጥ እቅድ አለው። የምክር ቤቱ ማረጋገጫ ፕሬዝደንት ዋታራን ቃለ-መሀላ አስፈጽሞ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ሀገሪቱን እንዲያስተዳድሩ ህጋዊ ይሁንታ የሚሰጥ ይሆናል።

አላሳን ዋታራ ባለፈው ሐሙስ የምርጫው አሸናፊ ይፋ ከተደረገ በኋላ ከፈረንሳይኛ ሰርቪስ የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኛ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገዋል። ዝርዝሩን ሳሌም ሰለሞን አቀርበዋለች። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የአይቮሪ ኮስት ፕረዚደንት ድህነትን በግማሽ ለመቀነስ እንደሚጥሩ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00

XS
SM
MD
LG