በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደርባን ፖሊስ መርማሪ ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው ጥቃት መልስ ሰጡ


የደቡብ አፍሪቃ ፓሊስ
የደቡብ አፍሪቃ ፓሊስ

ጆንሰን ማልዳን የታፈሰ አበበን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉ ያሉ መርማሪ መኰንን ናቸው። "እኔ በአሁኑ ተጠርጣሪዎቹን እያፈላለግሁ ነው የምገኘው። ሌላ መረጃ የለኝም" ብለዋል።

በደቡብ አፍሪቃ ደርበን ከተማ ዘነፎብያ (Xenophobia) ወይም በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ምክንያት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በመከታተል የደርበን ፖሊስ መርማሪ መልስ ሰጥተዋል። ጆንሰን ማልዳን የታፈሰ አበበን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉ ያሉ መርማሪ መኰንን ናቸው።

"መልካም፣ እኔ ተረኛ መርማሪ ጆንሰን ማልዳ ነኝ። ለአካባቢው የመደበ መኰንን ወደ ጣቢያ መጣና የሞተ ሰው አስከሬን መገኘቱን ነገረኝ። እኔም ወደተባለው ስፍራ ሄድኩ። እዚያውም፣ በሱቅነት በሚጠቀሙበት አንድ ኰንቴነር ውስጥ የሞተ ሰው ነበር። ኮንቴነሩ ለመግቢያና ለመውጫ የሚያገለግል በርና መስኮት አለው። ሰውዬው ቀደም ብሎ የሞተ እንጂ በሕይወት ኖሮ እንደተባለው ቤንዚን ተርከፍክፎበት አይደለም የሞተው። እኔ በአሁኑ ተጠርጣሪዎቹን እያፈላለግሁ ነው የምገኘው። ሌላ መረጃ የለኝም" ብለዋል።

ሳሌም ሰለሞን ጉዳዩን የያዙትን መርማሪ መኰንን ጆንሰን ማልዳን አነጋግራዋለች፣ አዲሱ አበበ አቅርቦታል። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የደርባን ፖሊስ መርማሪ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደረሰው ጥቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

XS
SM
MD
LG