በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ. ለኢትዮጲያ አስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ መደበ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) የአስቸኳይ መልስ ፋንድ ክፍል ሰርፍ(CERF) ለኢትዮጵያ ከገጠሙት ሁሉ የከፋ በሆነ ድርቅ ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ ትናንትና ሰጠ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኦቻ(OCHA) በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከገጠሙት ሁሉ የከፋ በሆነ ድርቅ ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ ትናንትና ሰጠ።

ይህ የመንግስታቱ ድርጅት የአስቸኳይ እርዳታ ሰጪ ክፍል ወይም ሰርፍ (CERF) በዓመት ለመላው ዓለም የሚደርስ $450 ሚልዮን ባጀት ያለው ሲሆን፣ እአአ በ2015 ወደ $80 ሚልዮን ዶላር፣ ኤል ኒኞ ላጠቃቸው አከባቢዎች ማለትም ኤስያ፣ ላቲን አሜሪካና የአፍሪቃ ቀንድ ሃገሮች ርድታ እንደሚውል የኦቻ(OCHA) አስቸኳይ ርዳታ ክፍል ሰርፍ(CERF) ዋና ጸሃፊ ሊሳ ዳውተን (Lisa Doughten) ገልጸዋል።

ከዚህ ባጀት ርዳታ በኢትዮጵያ ለደረሰው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት በሚወስዳቸው ርምጃዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና አጋሮቹ ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ሊሳ ዳውተን አስረድተዋል። $17 ሚልዮኑ እርዳታ የሚውልበትን ሁኔታም ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአስቸኳይ እርዳታ ሰጪ ክፍል ወይም ሰርፍ (CERF)

በኢትዮጲያ የበልጉ ዝናብ መቅረትን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ በኤል ኒኞ የተፈጠረው የአየር መመሳቀል በተጐዱ አካባቢዎች የምግብና የውሃ ዕጥረት መፍጠሩን ኦቻ (OCHA) እስታውቋል። የኢትዮጲያ መንግሥት በዚህ ዓመት ብቻ 8.2 ሚልዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጥሪ አቅርቧል። ይህ ከዚህ በፊት ከተሰጠው ቁጥር ከ2.9 ሚልዮን የላቀ መሁኑን ኦቻ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል። ወደፊትም ወደ 22 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች በአፍሪቃ ቀንድ ድርቅ ባስከተለው ችግር የእህል እጥረት እንደሚያጋጥማቸው፣ ከነዚህ 15 ሚልዮኑ ኢትዮጲያውያን እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች እና የአስቸኩዋይ ርዳታ ማስተባባሪያ ረዳት ዋና ጸሃፊ ስቴፈን ኦብራየን (Stephen O’Brien) በበኩላቸው ትላንት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ “ለዚህ አጣዳፊ ሁኔታ ወቅታዊ ምላሽ መስጠት ወሳኝ ነው። እአአ በቀጣዩ 2016 ዓ.ም. ችግሩ ይበልጡን የሚብስ በመሆኑ ዛሬ ፈጥነን ካልተንቀሳቀስን ነገ የከፋ ሁኔታ ይጠብቀናል” ብለዋል።

ከድርጅቱ ማዕከላዊ የአጣዳፊ እርዳታ ወጪ የሚሆነው ገንዘብ በድርቁ ለተጎዳው ሕዝብ ባስቸኩዋይ የሚያስፈልገውን ምግብ ለማቅረብ ይውላል ብለዋል። ገንዘቡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም 1.37 ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት እንዲሁም በተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ለተጎዱ 164,000 ሴቶችና ህጻናት ልዩ አልሚ ምግብ ለማቅረብ የሚያውል መሆኑንም ኣስረድተዋል።

ሰርፍ (CERF) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሃገሮች የሚያገኘውን ወደ $4 ቢልዮን የሚሆን አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እአአ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ እስከዛሬ ለ95 ሃገሮች እያቀረበ ይገኛል።

የኦቻ(OCHA) አስቸኳይ ርዳታ መልስ ሰጪ ክፍል ሰርፍ(CERF) ዋና ጸሃፊ ሊሳ ዳውተን (Lisa Doughten) በኢትዮጲያ የትኞቹ ክልልሎች ከፍተኛ እርዳታ እንደሚስፈልጋቸውና ርዳታው እንዴት እንደሚውል ከአሜሪዳ ድምጽ ጋር ተችተዋል። ቃለ-ምልልሱን ሳሌም ሰለሞን አጠናቅራለች ሙሉውን ዘገባ ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

የተ.መ.ድ. ለኢትዮጲያ አስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ መደበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00

XS
SM
MD
LG