በደቡብ ኢትዮጵያ ምሥራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖችንና ጌዴኦ ዞንን በሚያዋስኑ ወረዳዎች ውስጥ ግጭት አገርሽቶ የብዙ ዜጎች ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል።
በኢሮብ ወረዳ የደውሃን ከተማ ሕዝብ የአልጀርሱን ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰነውን ውሳኔ፣ በአደባባይ ተቃወመ፡፡
ጠንካራ ሃገራዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲያና ለፍትህ ፓርቲ መሪዎችና አባላት እንደተቀላቀሉት ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት /መድረክ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት የድርድር ጥያቄ እንዳቀረበላቸው አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት /መድረክ/ ሀገሪቱ ይበልጥ እንድትረጋጋ እና ወደ ተሻለ የለውጥ አቅጣጫ እንድትገባ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት በመመስረት እንዲተባበር ለኢህአዴግ ጥሪ አቀረበ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ሀና ማርያም በተባለው አካባቢ የመኖሪያ ቤታቸው በኃይል የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ያገኛል ተባለ።
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ሃና ማርያም ከተባለው አካባቢ ቤታችን በኃይል ፈርሶብናል ያሉ ነዋሪዎች ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡
ከትናንት በስቲያ ከእሥር የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀኃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋራ ያደረጉት ውይይት እጅግ አውንታዊ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ ከእሥር የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋራ ያደረጉት ውይይት እጅግ አውንታዊ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የዘገየው፣ ማረሚያ ቤቱ “ሰነድ አልደረሰኝም” በማለቱ እንደነበር ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እሥር ላይ የቆዩት የግንቦት ሰባት መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ይፈታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውሏል።
የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታን ጭምሮ፣ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ አያሌ ሰዎች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መጠየቁ ተሰማ፡፡
ሰሞኑን በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "ማንጎ ጨፌ" በሚባል አካባቢ ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች በኃይል መፍረሳቸውን መላው የኢትዮጵያ የአንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አስታወቀ፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሀገር ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ተጨባጭ ከሆነ የሕዝብ ኑሮ እድገት ጋር ሊያገናዝብ እንደሚገባ አመለከቱ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለይ ሐና ማርያም በተባለው አካባቢ ከ6 ሺህ ያላነሱ ቤቶች በመፍረሳቸው ተበደልን ያሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድን ትዛዝ ተከትሎ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ክስ ከመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ጨምሮ የሥልሳ ሁለት ተከሳሾችን ክስ አቋረጠ፡፡
የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን አደረሰ የተባለውን የአካባቢ ብክለትና የአስከተለውን ጥፋት በመቃወም ለሰልፍ በወጣ ሕዝብና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአዶላ ከተማ ከትናንት እስከ ዛሬ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ሰባት መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ