አዲስ አበባ —
የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን አደረሰ የተባለውን የአካባቢ ብክለትና የአስከተለውን ጥፋት በመቃወም ለሰልፍ በወጣ ሕዝብና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአዶላ ከተማ ከትናንት እስከ ዛሬ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ሰባት መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡
ዛሬ በከተማዋ መሃል የመከላከያ ሰራዊት መስፈሩንና ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለም ተነገረ፡፡ በአካባቢው በአጋዋዩ ወረዳ አይዲማ ከተማም ሕዝብ ለተመሳሳይ ተቃውሞ ወጥቶ እንደሰነበተ፣ የሚድሮክ ኩባንያ እንዲወጣ እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል የማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢ ፈቃድን ከዛሬ ጀምሮ ማገዱ ተሰማ፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ