አዲስ አበባ —
ሰሞኑን በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "ማንጎ ጨፌ" በሚባል አካባቢ ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች በኃይል መፍረሳቸውን መላው የኢትዮጵያ የአንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አስታወቀ፡፡ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በተፈፀመው ተደጋጋሚ ድርጊት መማረራችውንም ገልፀዋል፡፡ በአካባቢው አስተዳደር ክህድት እንደተፈፀመባችውም ይናገራሉ፡፡
ከአዲስ አበባ አስተዳደርም ሆነ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ዛሬም አልተሳካም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።