አዲስ አበባ —
ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የጣለበት ዕድል በከንቱ እንዳይባክን ሲል ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አሳሰበ፡፡
በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር መሪነት ከሚከናወኑ የለውጥ ዕርምጃዎች ተፃራሪ አንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ የመብቶች ጥሰት ድርጊቶች ያላቸውን ለዚህ ምሳሌዎች እንደሆኑም አመለከተ፡፡ ለውጡ በይበልጥ እንዲጠናከር ይወሰዱ ያላቸውን ዕርምጃዎችም ጠቁሟል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።