አዲስ አበባ —
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የመጀመሪያዎቹ 1መቶ የሥልጣን ቀናት ትልቁ ዲፕሎማሲያዊ ስኬታቸው፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም ሊያሰፍን የሚችል ስምምነት ማድረጋቸው እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሁለቱ ሕዝቦችና መሪዎቻቸው ለዚህ ጥረታቸውና ስኬታቸው ዓለምቀፍ ዕውቅና እንዲሰጣቸው እየተጠየቀ እንደሆነም የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ ቀናት በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ብዙ የውጭ ባለሃብቶች ወደ ሀገሪቱ እየገቡ መሆናቸውም ተገለጠ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ