የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ተዋጊዎች በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቃዊ ክፍል የምትገኘው ቺቦክ ከተማ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ወርረው ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ተማሪዎችን ጠልፈው ከወሰዱ ሁለት ዓመት ሞላ።
ከዚያ ወዲህ ሃምሳ ሰባቱ ልጃገረዶች ከጠላፊዎቻቸው እጅ ያመለጡ ሲሆን ሁለት መቶ አስራ ዘጠኙ እስካሁን አልተገኙም።
ፋይል ፎቶ - ከቦኮ ሃራም ቪድዮ የተገኘ
አዲስ ቪዲዮ ለወላጆቻቸው በህይወት አሉ የሚያሰኝ ተስፋ ፈንጥቋል
የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከሰሜን ምስራቋ ቺቦክ ከመንደር ከሁለት መቶ በላይ ልጃገረዶችን በጠለፈ በሁለት ዓመቱ ብቅ ያለ አዲስ ቪዲዮ ለወላጆቻቸው በህይወት አሉ የሚያሰኝ ተስፋ ፈንጥቋል።
Your browser doesn’t support HTML5
VOA60 Africa - New Video Shows 15 'Chibok Girls' But Parents Wary
ከአራት ወራት በፊት የተቀረጸ ነው ተብሎ በወጣው ቪዲዮ ላይ ያሉትን አብዛኞቹ ልጆች የማውቃቸው ናቸው ሲሉ አንዲት ተጠላፊዎቹ የመንደራችን ልጆች ናቸው ሲሉ እንዲት እናት ተናግረዋል።
የቺቦክ ልጃገረዶች የተጠለፉበትን ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በዋና ከተማዋ አቡጃ በተካሄደው “ልጆቻችንን አምጡልን“ የተባለው እንቅስቃሴ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙት አስቴር ያኩቡ እንባ እየተናነቃቸው፣ "ትክክል ነው። ቪዲዮው ላይ ያሉት እነሱ ናቸው። ዕርግጥ ተለውጠዋል። የዛሬ ሁለት ዓመት እንደዚህ አልነበሩም፣ አድገዋል። ግን እነሱ ናቸው።" ብለዋል።
የናይጄርያ ወታደሮች በቺቦክ ከተማ
ቦኮ ሃራም ከቺቦኩ አዳሪ ትምህርት ቤት ስለጠለፋቸው 219ኙ ልጃገረዶች ከተወሰዱበት ጊዜ አንስቶ የት እንዳሉ ሳይታወቅ የከረመ ሲሆን ትናንት የወጣውና በታህሳስ ወር የተቀረጸ ነው የተባለው ቪዲዮ አስራ አምስቱ ልጃገረዶች ይታዩበታል።
በቪዲዮው ልጃገረዶቹ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ለሚቀርብላቸው ጥያቄ በሃውሳና በኪባኩ ቋዋንቋዎች ስማቸውንና ከየት እንደተጠለፉ ሲናገሩ ይሰማሉ።
ቦኮ ሃራም 276 የቺቦክ ከተማ ልጃገረዶች ተማሪዎችን ጠልፈው ከወሰዱ ሁለት ዓመት ሞላ
የሀገሪቱ የማስታወቂያና የባህል ሚኒስትር ላኢ ሞሃመድ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሲ ኤን ኤን (CNN) ቴሌቪዥን የወጣውን ቪዲዮ ጥርጣሬ አድሮባቸዋል። መንግስታቸው ልጆቹ ያሉት እዚህ ነው የሚሉ የተሳሳቱ ጥቆማዎች በተደጋጋሚ ደርሶታልናም ብለዋል።
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ክሪስ ስታይን (Chris Stein) ቺቦክ ኢምባላላ ከተማ ከተጠለፉት ልጃገረዶች የአራቱን ወላጆች አነጋግሯል። ባልደረባችን ቆንጂት ታየ ያዘጋጀችውን ዝርዝር ለማዳመጥ፣ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5
የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም የቺቦክ ከተማ ልጃገረዶችን ጠልፈው ከወሰዱ ሁለት ዓመት ሞላ