No media source currently available
የናይጄሪያው ጽንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ተዋጊዎች በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቃዊ ክፍል የምትገኘው ቺቦክ ከተማ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ወርረው ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ተማሪዎችን ጠልፈው ከወሰዱ ሁለት ዓመት ሞላ። ከዚያ ወዲህ ሃምሳ ሰባቱ ልጃገረዶች ከጠላፊዎቻቸው እጅ ያመለጡ ሲሆን ሁለት መቶ አስራ ዘጠኙ እስካሁን እልተገኙም።