በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን ፓርቲውና የዴሞክራቲክ እጩዎች ምርጫ ሂደት እየተጠናቀቀ ይመስላል

የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩና የቢልዮኖች ዶላሮች ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ /ፎቶ ሮይተርስ/
የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩና የቢልዮኖች ዶላሮች ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ /ፎቶ ሮይተርስ/

በትናንቱ የኢንድያና ጠቅላይ ግዛት የፓርቲዎቹ ምርጫ ወደ ፖለቲካው አለም በቅርቡ የገቡት የቢልዮኖች ዶላሮች ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ ተቀናቃኞቻቸውን ቴድ ክሩዝንና ጃን ኬስክን በቀላሉ ዘርረዋል ማለት ይቻላል።

በዩናትድ ስቴትስ ለፕሬዝደንትነት እየተካሄደ ያለው የሁለቱ ፓርቲዎች፣ የሪፓብሊካን ፓርቲውና የዴሞክራቲክ እጩዎች ማንጠርያ ምርጫ ሂደት እየተጠናቀቀ ይመስላል። ቀዳሚዎቹ የፓርቲያቸውን ምርጫ ሳያረጋገጡ አልቀሩም፣ በሁለቱም ፓርቲዎች ማለት ነው።

የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩ ጃን ኬስክ
የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩ ጃን ኬስክ

በትናንቱ የኢንድያና ጠቅላይ ግዛት የፓርቲዎቹ ምርጫ ወደ ፖለቲካው አለም በቅርቡ የገቡት የቢልዮኖች ዶላሮች ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ ተቀናቃኞቻቸውን ቴድ ክሩዝንና ጃን ኬስክን በቀላሉ ዘርረዋል ማለት ይቻላል።

የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩ ቴድ ክሩዝ
የሪፓብሊካን ፓርቲው እጩ ቴድ ክሩዝ

የትራምፕ ሪፓብሊካን ተቀናቃኞች አስፈላጊውን የተወካዮች ድምጽ በአስተማማኝ ሁኔታ ባለማግኘታቸውም ዘመቻቸውን አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል። ብዙዎች ተንታኞች የትናንቱን ምርጫ ውጤት ለትራምፕ በዝረራ እንደማሸነፍ ነው የወሰዱት፣ ሁለቱም ቴድም ኬሲክም ተሰናበቱ።

የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሂላሪ ክሊንተን
የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሂላሪ ክሊንተን

በዴሞክራቶቹም በኩል ምንም እንኳን በርኒ ሳንደርስ ትናንት በአነስተኛ የድምጽ ልዮነት ቢያሸንፉም የቀድሞዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተንን የፓርቲያቸውን ውክልና በማግኘት ለፕሬዝደንትነት ተወዳዳሪ የመሆናቸው ነገር ግን የሂላሪ እጩነት ይበልጥ እየተረጋገጠ የመጣ ይመስላል።

ባልደረቦቻችን ከየስፍራው ያደረሱን ዘገባዎች አሉ፣ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል።

በዩናትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን ፓርቲውና የዴሞክራቲክ እጩዎች ምርጫ ሂደት እየተጠናቀቀ ይመስላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00

XS
SM
MD
LG