በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ለፕሬዘዳንትነት እየተካሄደ ባለው ውድድር የሁለቱ ፓርቲዎች ቀዳሚ እጩዎች በምዕራባዊ ግዛቶች አሸንፈዋል


ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ (Donald Trump) የቴክሳሱን ቴድ ክሩዝ (Ted Cruz) ከ 20 በላይ ነጥብ በማግኘት በቀላሉ ያሸነፉት በአሪዞና (Arizona) ሲሆን የ 58ቱንም ተወካዮች ድምፅ ጠቅልለው ወስደዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ለፕሬዘዳንትነት እየተካሄደ ባለው ውድድር ትላንት በሁለቱ ፓርቲዎች ውስጥ ቀዳሚዎቹ እጩዎች በምዕራባዊ ግዛቶች አሸንፈዋል።

ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ (Donald Trump) የቴክሳሱን ቴድ ክሩዝ (Ted Cruz) ከ 20 በላይ ነጥብ በማግኘት በቀላሉ ያሸነፉት በአሪዞና (Arizona) ሲሆን የ 58ቱንም ተወካዮች ድምፅ ጠቅልለው ወስደዋል።

ክሩዝ በዩታ ከግማሽ በላይ ድምፅ አሸንፈው የ 40 ተወካዮችን ድምፅ በመሰብሰብ ማንሰራራት ችለዋል።

ዲሞክራቷ ሂላሪ ክሊንተን ( Hillary Clinton) አሪዞና ላይ ሳንደርስን ያሸነፉት በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ነው። 1681 ለ 927 ይመራሉ በተወካዮች ድምፅ። ዶናልድ ትራምፕ አስፈላጊውን 1237 የተወካዮች ድምፅ በማግኘት ለፕሬዘዳንትነት የሪፐብሊካን ፓርቲውን መወከል እንዳይችሉ ለማድረግ፥ የኦሃዮ አስተዳዳሪ ጆን ኬስክ (John Kasich) እና ሴናተር ተድ ክሩዝ (Ted Cruz) ከባድ ጥረት ይዘዋል።

ያሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ክሪስ ሃንስ (Chris Hannas) የትላንቱን ቅድመ-ምርጫ አጠቃላይ ውጤት አጠናቅሯል።

ሰሎሞን ክፍሌ ለ”ዲሞክራሲ በተግባር” ዝግጅቱ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG