በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴይትስ ምርጫ 2016 “ታላቁ ማክሰኞ”


“Super Tuesday” በዩናይትድ ስቴይትስ የፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሞት የሽረት ማክሰኞ የመጀመሪያ ዙር ፉክክሩ ላይ ወሳኝ ቀን ናት።

“እኩል ለሰራንው ስራ እኩል ደመወዝ መከፈያችን ጊዜ አሁን አይደለም ትላላችሁ? በመካከላችን የሰፈነውን ጥላቻ ማስወገጃ ጊዚያችን አሁን ነው።

በስርዓት ደረጃ የሰፈነ ዘረኝነት መወገጃው ወቅት አሁን ነው፤ ማህበረሰቦች ወደኋላ እንዲቀሩ የሚያደርጉ መዋቅሮች መቀየር አለባቸው።” ብለዋል ክሊንተን።

“Super Tuesday” በዩናይትድ ስቴይትስ የፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሞት የሽረት ማክሰኞ የመጀመሪያ ዙር ፉክክሩ ላይ ወሳኝ ቀን ናት።

ሪፐብሊካኑ በ13 ግዛቶች የቅድመ-ምርጫና ኮከስ ሲያካሂዱ ዴሞክራቶቹ ደግሞ በ12 ግዛቶች ምርጫዎች ያከናውናሉ።

በማክሰኞው የመጀመሪያ ዙር የዩናይትድ ስቴይትስ የፕሬዝደንታዊ ምርጫ የቴክሳስ ግዛት አቢይ የአትኩሮት ማእከል ትሆናለች። የቴክሳስ ግዛት በሪፐብሊካኑ ፓርቲ ምርጫ 155 ወኪል/እንደራሴዎች (ዴሊጌትስ) አላት።

በአጠቃላይ የሪፐብሊካኑ ፓርቲ እጩ ለመሆን የሚያስፈልገው የእንደራሴዎች ቁጥር 1237 ሲሆን ለዴሞክራቶቹ ደግሞ 2383 ነው።

በታላቁ ምክሰኞ በሚካሄደው ቅድመ-ምርጫ ወደ ግማሽ የሚጠጉት እንደራሴዎችን ለማግኘት ነው እጩዎች የሚፎካከሩት።

በዩናይትድ ስቴይትስ ምርጫ ህዝቡ የሚሰጠው ድምጽ፤ በወኪል/እንደራሴዎች ቁጥርና ድምጽ ነው የሚወሰነው።

በቴክሳስ የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕና ቴድ ክሩዝ፤ ምንም እንኳን በፖለቲካ አመለካከታቸው ባይራራቁም፤ ፉክክራቸው ተጣጡፏል። አንዳንድ የህዝብ አስተያየት አሃዞች እንደሚያመለክቱት በቴክሳስ ሴናተር ቴድ ክሩዝ በሰፊ ልዩነት እይረመሩ ነው። በአጎራባቿ አርካንሶ ግዛትም በጥቂት ልዩነት ይመራሉ። በሌሎች ግዛቶች ግን ዶናልድ ትራፕ በመምራት ላይ ናቸው።

ቴድ ክሩዝ በሴኔቱ የሚወክሉትም ቴክሳስን ስለሆነ፤ የሚወዳደሩት በሜዳቸው ነው። በማክሰኞለቱ የዩናይትድ ስቴይትስ የመጀመሪያ ዙር የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሳይጠበቁ ግን የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ የመጡት ዴሞክራቱ በርኒ ሳንደርስና ዶናልድ ትራምፕ እንደሆኑ በራይስ ዩኒቨርስቲ (Rice University) የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ማርክ ጆንስ ይናገራሉ። “በተለያዩ ምክንያቶች በዋሽንግተን ዲሲ የቆዩ ፖለቲከኞችን ውሳኔ አለመስጠት አሜሪካዊያን መራጮች አጥብቀው ጠልተዋል።

ሳንደርስና ትራምፕ የቆዩ የፖለቲካ ባህሎችን እናስቆማለን ሲሉ፤ ህዝቡ እያዳመጣቸውና ድምጹንም እየሰጣቸው ይገኛል።” ሴናተር ማርኮ ሩቢዮም በፉክክሩ ለመቀጠል የሚያስችላቸው ድምጾችን እንደሚያገኙ ተንታኞች ያስረዳሉ።

በሂውስተን ቴክሳስ በሂላሪ ክሊንተን የምረጡኝ ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ሰዎች በጣም ብዙና ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ያሰሙ የቴክሳስ ግዛት ነዋሪዎች የተገኙበት ነበር። በቴክሳስና በሌሎች አካባቢዎች መራጮች ጆሯቸውን ለቨርመንቱ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ ሰጥተዋል። “ባለፉት 30 ዓመታት የሀገር ሀብት ክፍፍል በፍጥነት ሲከናወን ቆይቷል። ሆኖም የሀብት ክፍፍሉ እየሔደ ያለው ባልተፈለገው አቅጣጫ ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ የገቢ አለመመጣጠንን አስመልክቶ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

የበርኒ ሳንደርስ የምረጡኝ ዘመቻ ቁልፍ ፖሊሲ የሀገሪቱ አብዛኛው ሀብት በ0.1% ሀብታሞች እጅ መሆኑን ማስቆም፤ የመካከለኛ ገቢ ያላቸው አሜሪካዊያን የምጣኔ ሀብት ድርሻቸውን ማስፋት የሚል ነው።

የዩናይትድ ስቴይትስ ምርጫ 2016 “ታላቁ ማክሰኞ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG