በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትላንቱ የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዝዳንታዊ ቅድመ ምርጫ ውጤቶችና አንድምታ


ይህ ድንቅ ታላቅ ምሽት ነው። ዶናልድ ትራምፕ። “ለሌሎች ሃሳብ ደንታ ቢስ በመሆንና በድንፋታ ፋንታ አንዳችን ለሌላችን በአክብሮት፥ በትህትናና በፍቅር ብንቀርብ፤ አንዳችን ሌላችንን ከመጣል አንዳችን ሌላችንን ከፍ ብናደርግና ብናነሳ፤ ተባብረን ከዳር የማደርሰው ነገር አይኖርም።” ሴናተር ሂላሪ ክሊንተን።

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንታዊ ቅድመ ምርጫ የየፓርቲዎቻቸው እጩ ሆኖ ለመቅረብ የሪፐብሊካንና የዲሞክራቲክ ተፎካካሪዎች በትላንትናው ዕለት በተካሄዱት ምርጫዎች ወሳኝ ከሆነ ምዕራፍ የደረሱ ይመስላል።

Number of pledges delegates for each candidate, as of March 16, 2016
Number of pledges delegates for each candidate, as of March 16, 2016

የሪፑብሊካኑ ግንባር ቀደም ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ (Donald Trump)እና ዲሞክራቷ ሂላሪ ክሊንተን (Hillary Clinton)ከፍተኛውን የድምፅ ብልጫ በማግኘት አሸናፊዎች ሆነዋል።

በተለይ Trump በፍሎሪዳ ማሸነፋቸው፥ ከሦሥቱ ተቀናቃኞቻቸው አንዱ የሆኑትን የፍሎሪዳውን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ሴናተር ማርኮ ሩብዮን (Marco Rubio) ከምርጫ ውድድሩ ውጭ አድርገዋቸዋል።

ተፎካካሪዎቹ በእስካሁኑ የምርጫ ሂደት ያስመዘገቧቸውን አለያም ማስመዘገብ የተሳናቸውን ውጤት ተንተርሰን የቅድመ ምርጫውን ውጤት ምንነትና አድምታ እንመረምራለን።

ለሞያዊ ትንታኔው በዊስኮንሰብ ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዶ/ር ዳንኤል ተፈራን ጋብዘናል።

የትላንቱ የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዝዳንታዊ ቅድመ ምርጫ ውጤቶችና አንድምታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG