በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩዋንዳ የህገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ድምፅ አሰጣጥ ሊካሄድ ነው


የሩዋንዳው ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ በቀጣዩ እአአ 2017 ለ3ኛ ጊዜ ሊመረጡ ይችሉ እንደሆን ለመወሰን፣ በቀጣዩ ሳምንት የህገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ድምፅ አሰጣጥ እንደሚካሄድ ገለጹ።

የሩዋንዳው ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ በቀጣዩ 2017 ለ3ኛ ጊዜ ሊመረጡ ይችሉ እንደሆን ለመወሰን፣ በቀጣዩ ሳምንት የህገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ድምፅ አሰጣጥ እንደሚካሄድ ገለጹ።

የሩዋንዳ መንግሥት ዛሬ ረቡዕ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ ከሩዋንዳ ውጪ ለሚኖሩ ዜጎች ውሳኔ-ሕዝቡ የሚካሄደው በመጪው ታኅሣሥ 1 ቀን እአአ 2008 ዓም ሲሆን፣ እዚያው ሩዋንዳ ላሉ ነዋሪዎች ደግሞ ታኅሣሥ እአአ 2, 2008 ነው።

ውሳኔ-ሕዝቡ የሚጠይቀው፣ የአንድ ፕሬዚደንት የሥልጣን ዘመን ከሰባት ወደ አምስት ዓመት ዝቅ እንዲል የቀረበን ማሻሻያ ለማጽደቅ ሲሆን፣ እአአ ከ2000 ዓ.ም. ጀምረው ሥልጣን ላይ ለቆዩት ለፕሬዚደብት ካጋሜ ግን ልዩ አስተያየት ያደርጋል።

አሁን ሥራ ላይ ባለው በወቅቱ ህግ መሠረት፤ ካጋሜ እአአ በ2017 ሥልጣን እንዲለቁ ይደነግጋል። በማሻሻያ ህጉ ግን ለሦስተኛ የሰባት ዓመት ጊዜ እንዲወዳደሩ፣ ከዚያ ለሁለት ተከታታይ አምስት ዓመት እንዲወዳደሩ ይፈቅዳል።

ውሳኔ-ሕዝቡ በቀላሉ ማለፍ እንደሚችል ከወዲሁ ተተንብዮአል። ዘገባችንን ለማዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በሩዋንዳ ህገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ድምፅ አሰጣጥ ሊካሄድ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:32 0:00

XS
SM
MD
LG