በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሩንዲው ግጭትና አካባቢውን እያሰጋ ያለው ውጥረት


ግጭቱ ከመቀስቀሱ አስቀድሞም በቋፍ የነበረው የተጎራባቾቹ ብሩንዲና ሩዋንዳ ግንኙነት ከባሰ ውጥረት ከመግባቱም ባሻገር አንዱ የሌላውን ባለጋራ ያግዛል በሚል መወነጃጀል ይዘዋል።

ፕሬዝዳንት ፒሬ ንኩሩንዚዛ (Pirrie Nkurunziza) አገሪቱን ለሦሥተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን ለመምራት በእጩነት ቀርበው መወዳደር መወሰናቸውን ይፋ ካደረጉበት ካለፈው ሚያዝያ ወር አንስቶ በተቀሰቀሰው ቀውስ እየታመሰች ያለችው ብሩንዲ ግጭት በድንበሯ ብቻ የሚወሰን አልሆነም።

ወደ ጎረቤት ሩዋንዳ የተዛመተው ውጥረት እያደረ ቀስ-በቀስ እየናረ የመጣ ይመስላል።

ጂል ክሬግ (Jill Craig) ከናይሮቢ ለአሜሪካ ድምጽ ያጠናቀረችው ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል። ይህንን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የብሩንዲው ግጭትና አካባቢውን እያሰጋ ያለው ውጥረት /ርዝመት - 4ደ43ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:42 0:00

XS
SM
MD
LG