በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር እንደሚፈልጉ አስታወቁ


የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ እ አ አ በ2017 ዓ. ም. ለሶስተኛ የስልጣን ጊዜ ለመወዳደር እንደሚፈልጉ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:04 0:00

የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ እ አ አ በ2017 ዓ. ም. ለሶስተኛ የስልጣን ለመወዳደር እንደሚፈልጉ አስታወቁ

የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ እ አ አ በ2017 ዓ. ም. ለሶስተኛ የስልጣን ለመወዳደር እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

ካጋሜ ይህን ያስታወቁት በህገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ ከኣንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው ውሳኔ ህዝብ የተሰጠው ድምጽ እንዲወዳደሩ ከፈቀደላቸው በኋላ መሆኑ ነው።

ካጋሜ ዛሬ በቴለቭዥን በተላለፈው የአዲስ ዓመት ንግግራቸው “ጉዳዩን ይህን ያህ ክብደትና ትኩረት ስለሰጣችሁት፣ እኔ ያለብኝ መቀበል ብቻ ነው ማለታቸው ተጠቅሷል። አክለውም ሃጋራችን የዕድሜ ልክ ፕሬዚደንት አትፈልግም እኔም ያን አልፈልግም ሲሉ ብለዋል።

የሩዋንዳው ፕሬዚደንት የስልጣን ዘመን የሚያበቃው በ2017 ሲሆን በህግ መንግስት ማሻሻያው መሰረት የሃምሳ ስምንት ዓመቱ መሪ ለሰባት ኦኣመትየስልጣን ዘመን ይወዳደሩና ከዚይ በተከታታይ ለሁለት የአምስት ዓመት የስልጣን ዘመን ይቀጥላሉ እስከ ሁለት ሺህ ሰላሳ ኣራት መንበረ ስልጣኑ ላይ ሊኖሩበት ይችላሉ ማለት ነው።

ባለፈው ሳምንት በተካሄደ ውሳኔ ህዝብ ዘጠና ከመቶው መራጭ የህገ መንግስት ማሻሻያውን ደግፎ ድምጹን ሰጥቱዋል። ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት በበኩላቸው ማሻሻያዎቹ የሀገሪቱን ዲሞክራሲ ይሸረሽራሉ ሲሉ ነቅፈዋል። የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ለሶስተኛ የስልጣን ለመወዳደር እንደሚፈልጉ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00

XS
SM
MD
LG