የርዋንዳ ፕረዚደንት ፖል ካጋሜ ሀገሪቱ የፕረዚዳንትን የስልጣን ጊዜ የሚገድበውን ህገ-መንግስት ለመለወጥ በመወስናዋ አመስግነዋል። ይሁንና እንደገና ለመመረጥ ይወዳደሩ እንደሆነ አልተናገሩም።
ፕረዚዳንት ካጋሜ ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ባቀረቡት አመታዊ ንግግር “ማንም ለዘላለም የሚኖር ሰው የለም። ይሁንና በእሴት፣ በተቋማትና በመሻሻል ላይ የጊዜ ገደብ ሊኖር አይችልም” ብለዋል። ሃላፊነቱን ከአንድ የመንግስት አገልጋይ ወደ ሌላ ለማስተላለፍ በሚያስፈልግበት ጊዜ እንደሚከናወን ርውናዳውያን ይተማመናሉ” ሲሉም አክለውበታል።
የርዋናዳው መሪ የስልጣን ጊዜ ከሁለት አመታት በኋላ ያበቃል። ይሁንና አዲሱ ህገ-መንግስታዊ ለውጥ የ 58 አመት እድሜው ካጋሜ ለሌላ ሰባት አመታታ የስልጣን ጊዜ እንዲወዳደሩ ያስችላቸዋል። ለሁለት የአምስት አመታት የስልጣን ጊዚያትም ሊወዳደሩ ይችላሉ። በአጠቃላይ እአአ እስከ 2034 አም ስልጣን ላይ ሊቆዩ ይችላሉ።
ህገ-መንግስቱን ለመለወጥ ወይም ላለመለወጥ ባለፈው አርብ በተካሄደው ረፈረንደም ወይም ህዝበ-ውሳኔ ከተሰጣው ድምጽ 98 ከምቶ የሚሆኑት ህገ-መንግስቱ እንዲለወጥ መርጠዋል።
የዩናትድ ስቴትስ (United States) እና የአውሮፓ ህብረት በማእከላዊት አፍሪቃይቱ ሃገር ዲሞክራሲን ያዳክማል በማለት ህገ-መንግሱቱን የመለወጥ ውሳኔን ነቅፈዋል። ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።