በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩዋንዳ መንግሥት አገሩ የሚገኙ የቡሩንዶ ስደተኞችን ወደ ሌላ ስርፋ እንደሚያዛውር አስታወቀ


የብሩንዲ ስደተኞች
የብሩንዲ ስደተኞች

ሩዋንዳ የቡሩንዲ ስደተኞችን ለማዘዋወር የወሰነችው "የሩዋንዳ ባለሥልጣናት የቡሩንዲ ስደተኞችን በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ላይ ያሳምጻሉ" በማለት የዩናይትስ ስቴትስ ዲፕሎማቶች በመናገራቸው መሆኑ ዘገባዎች ይጠቅሳሉ።

የሩዋንዳ መንግሥት አገሩ ውስጥ የሚገኙ የቡሩንዶ ስደተኞችን ወደ ሌላ ስርፋ እንደሚያዛውር አስታወቀ፤ ምክንያት፣ "የሩዋንዳ ባለሥልጣናት የቡሩንዲ ስደተኞችን በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ላይ ያሳምጻሉ" በማለት የዩናይትስ ስቴትስ ዲፕሎማቶች በመናገራቸው።

ሩዋንዳ ዛሬ ዐርብ ይህን ባስታወቀቸት ወቅት፣ "አገራቸው ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ነውጥ በመሸሽ ወደ ሩዋንዳ የመጡ የቡሩንዲ ስደተኞችን በወጉ ለማስተናገድ፣ የቡሩንዲ መንግሥት ከዓለአቀፍ ማኅበረሰብ ሸሪኮቹ ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃደኛ" መሆኑን ገልጻለች።

የስደተኞችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቷን በውል እንደምትገነዘብ ሩዋንዳ በዛሬው መግለጫዋ ጠቅሳ፣ እነዚህን ስደተኞች ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ወገን እስካሁን አለመቅረቡንም አልሸሸገችም።

XS
SM
MD
LG