በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የርዋንዳ የዘር ፍጅት ከተጫረ 21 ዓመት ሆነ


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ለስምንት መቶ ሺህ ሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው የርዋንዳው ፍጅት የተጀመረበትን መጋቢት 29 በመዘከር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙን ያ ታሪክ እንዳይደገም የሚያሳስቡ መልዕክቶችን ዛሬ አውጥተዋል፡፡

ዕለቱን አስመልክቶም ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጉድለቶች የተባሉ ግኝቶችን የያዘ ሪፖርት የወጣበት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባወጡት መግለጫ “… እንዲያ ዓይነቱን የጭካኔ ጅምላ ጭፍጨፋ ለማስቆም አብረን እንደምንሰለፍ፣ እነዚያ ቀኖች ዳግም እንዳይመለሱ “ሁለተኛ!” ብለን በፅናት እንምንቆም የምናረጋግጥበት ነው…” ብለዋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ደግሞ “… ድርጅቱ ሰባኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዚህ ዓመት እንዲህ ዓይነቱን ዕለት በሰቀቀን የመዘከራችን ትርጉም ከእንዲህ ዓይነቱ ያለፈ ታሪካችን ተነስተን የዛሬን ፈተናዎች እንድንጋፈጥና ያ ቀን ዳግም እንዳይመለስም በፅናት እንድንቆም ያሳስበናል” ብለዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG