በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤል ኒኞ የአየር ለውጥ በአፍሪቃ፣ በኤስያና በአሜሪካ ሀገሮች ድርቅ ማስከተሉ ተገለጸ


በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ
በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ

በርካታ የኤስያ፣ የአፍሪቃና የአሜሪካ ክፍሎች ኤል ኒኞ በተባለው የአየር ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ የአየር ሙቀት ገጥሟቸዋል። በየሶስትና ስድስት አመታት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ጠለል ላይ የሚከሰተው የውኃ ሙቀት ጽንፍ የአየር ሁኔታን ያስከትላል። የአየር ለውጡ በሚያስከትለው ድርቅ ክፉኝ የሚጎዱትም ከሰሀራ በመለስ ያሉት የአፍሪቃ ሀገሮች ናቸው።

ሶማሊላንድ ደሀ ከሚባሉት የአፍሪቃ ክፍሎች አንዷ ናት። በገጠር አከባቢ የሚኖሩት ሰዎች ኑሯቸውን ለማሻሻል ደፋ ቀና ይላሉ። ድርቅ ሲታከልበት ግን ከባድ ይሆንባቸውል።

መሐምድ ዑመር የተባሉ አርሶ አደር ስለኑሯቸው ይገልጻሉ።

መሐምድ ዑመር የተባሉ አርሶ አደር
መሐምድ ዑመር የተባሉ አርሶ አደር

“እድሜየ 80 ነው። በ 80 አመታት ሂወቴ እንዲህ አይነት ድርቅ አይቼ አላውቅም። ብዙ እንስሳትን ገድሎ ከፍተኛ ረሀብ አስከትሏል። ስለሆነም አደጋ ላይ ወድቀናል” ነበር ያሉት።

በጎረቤት ፑንትላንድና በኢትዮጵያ ክፍሎችም ተመሳሳይ የድርቅ ሁኔታ ተከስቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማልያ ክፍሎች በድርቅ በተመቱ አከባቢዎች የሚኖሩ 1.7 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎችን ለማትረፍ በአስቸኳይ ረድኤት እንዲቀርብ ጥሪ አድርጓል። ፒተር ክለርክ (Peter De Clercq) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ረድኤት አስተባባሪ ናቸው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ረድኤት አስተባባሪ ፒተር ክለርክ (Peter De Clercq)
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ረድኤት አስተባባሪ ፒተር ክለርክ (Peter De Clercq)

“ማኅበረሰቦች ለህልውናቸው የሚያስፈልገውን ነገር እያጡ ነው። የሰዎች በረሀብ መሞትንና ሰደትን ማቆም አለብን። ሰዎች ምግብና ውሀ እንዲሁም ገቢ ፍለጋ ከመሰደደ በስተቀር ሌል አመራጭ እያጡ ነው።”ብለዋል።

በኢትዮጵያም እንደዚሁ አንዳንድ ገበሬዎች ከረሀብ ለመትረፍ ድንበር ተሻግረዋል። ሀዋ ራያብ የተባሉ ሴት ስለድርቁ ሁኔታ ያብራራሉ።

ሀዋ ራያብ የተባሉ ሴት ስለድርቁ ሁኔታ እያብራሩ
ሀዋ ራያብ የተባሉ ሴት ስለድርቁ ሁኔታ እያብራሩ

“ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ ከገባ ሶስትኛ አመቱ ነው። ድንበሩን ሻገር ብሎ የግጦሽ ቦታ እንዳለ ተነግሮን ነበር። እዛ ስንደርስ ግን ያገኘነው ነገር የለም” ነው ያሉት ሀዋ ራያብ።

በህዝብ ብዛት ከአፍሪቃ ሁለተኛውን ቦታ የምትይዘው ኢትዮጵያ በብዙ አስርተ-አመታት ውስጥ ያልታየ አይነት ከባድ ድርቅ ገጥሟታል። የሀገሪቱ መንግስት 10 ሚልዮን የሚሆኑ በድርቁ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት አለም አቀፍ ረድኤት እየጠየቀ ነው። ባለፈው አመት ከደረሰባት የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ገና ያላገገመችው ማላዊም ከባድ የምግብ እጥረት ገጥሟታል። ማላዊትዋ ሊሳ ፋቺ ያብራርሉ።

“ከጎርፍ መጥለቅለቁ አደጋ በፊት ልጄ ደህና ነበር። እህላችንን ካጣን በኋላ ግን ልጄ ታሞ በምግብ እጥረት ተጎዳ። ወደ ሆስፒታሉ የመጣሁትም ህክምናና ምግብ ፍለጋ ነው” ይላሉ ሊሳ ፋቺ።

የማላዊ ፕረዚዳንት የብሄራዊ ቀውስ አዋጅ አውጀዋል። ሆኖም በአጠቃላይ በከፊል የአፍሪቃ ሀገሮች የተከሰተው የምግብ ቀውስ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል ጆሀን ሄፊንክ ጠቁመዋል።

ጆሀን ሄፊንክ
ጆሀን ሄፊንክ

“ገና ዋናው ቀውስ ይመጣል። ስለሆነም ሁኔታዎች ከመሻሻላቸው በፊት የባሰውን ሁኔታ የምናይ ይመስለኛል።” ብለዋል።

በድርቅ በተጎዱት አከባቢዎች ያሉት ሰዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ የሚተማመኑት በረድኤት ላይ በመሆኑ እርዳታ በፍጣነት እንዲደርስ ጥሪ እየተደረገ መሆኑን ባለሙያዎች አስገንዝበዋል።

የአየር ለውጡ በሚያስከትለው ድርቅ ክፉኝ የሚጎዱት ከሰሀራ በመለስ ያሉት የአፍሪቃ ሀገሮች እንደሆኑ የአሜሪካ ድምጽ ረድዮ ዘገቢ ዝላቲካ ሆክ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የኤል ኒኞ የአየር ለውጥ በአፍሪቃ፣ በኤስያና በአሜሪካ ሀገሮች ድርቅ ማስከተሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG