በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ. የ 90 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ 700 ሚሊዮን ዶላርስ በላይ ለማሰባሰብ ያለውን እቅድ አስታውቋል


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትናንትናውለት የጀመረው የዘጠና ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ 700 ሚሊዮን ዶላርስ በላይ ለማሰባሰብ ያለውን እቅድ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 10.2 ሚሊዮን ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠው ድርቅ፤ ያስከተለው ጉዳይ አነስተኛ ቢሆንም የዝናብ እጥረቱ ግን ከ1977ቱ የከፋ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትናንትናውለት የጀመረው የዘጠና ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ 700 ሚሊዮን ዶላርስ በላይ ለማሰባሰብ ያለውን እቅድ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት የበልግ ዝናብ በከፊል መጥፋትም የዜጎችን የምግብ ዋስትና ክፉኛ መፈታተኑን በአዲስ አበባ በመንግስታቱ ድርጅት የUN- OCHA ቃል አቀባይ ቾይዝ ኦኮሮ አስረድተዋል።

ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና የምግብ እጥረት ሁናቴ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ነበር
ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና የምግብ እጥረት ሁናቴ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ነበር

ከአንድ ወር በፊት ይጀምራል ተብሎ ተጠብቆ ለነበረው የበልግ ወቅት፤ ገበሬዎች ለመዝራት እንዲችሉ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት 4ሚሊዮን ዶላርስ የሚያወጣ ዘር እንደሚያከፋፍል አስታውቆ ነበር። እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ከአዲስ አበባ ልኳል።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG